ኮሮና ቫይረስ በዓለም ደረጃ ከ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሊያጠቃ ይችላል

0
298

ኮሮና ቫይረስ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2019 መጨረሻ በቻይናዋ ግዛት ውሀን ከተማ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ አለምን ስጋት ላይ የጣለ ከስተት ሁኗል፡፡ የኮሮና ቫይረስ በአለማችን መከሰት ተከትሎ የዓለም ፖለቲካዊ ኢኖሚያዊና እንዲሁም አጠቃላይ ሀይል አሰላለፍ መቀየሩ ግልፅ እየሆነ ነው፡፡ አሁን በኮሮና ቫይረስ  ፊት ሀያል ፣ ጠንካራ ፣ ያደገች ፣ ደሀ አልያም ኋላ ቀር የምትባል አገር የለችም ፤ሀገራት ጥንካሪያቸው ቫይረሱ ከመግታት አንፃር ብቻ ሁኗል፡፡

እስካሁን ኮሮና ቫይረስ 204 ሀገራት አዳርሷል፤እንዲሁም በሁለት ግዙፍ መርከቦች ማለትም በጃፓን እና በአሜሪካ መርከቦች ውስጥም ተገኝትዋል፡፡

በአሁኑ ሰአት በዓለማችን በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚልዮን በላይ ደርሷል፡፡ ከዚህ ቁጥርም አሜሪካ 245,373 የታማሚ ቁጥር ያለባት ሀገር በመሆን ከአለም ቀዳሚ ስትሆን ፣ጣልያን 115,242 በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ያላት በመሆን ከአለም ሁለተኛ ናት፡፡

እስካሁን በአለም ደረጃ ጣልያን ከፍተና ቁጥር  ዜጋ የሞተባት ሀገር ሆናለች፡፡ ጣልያን እስካሁን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከ13,000 በላይ ዜጎቿን አጥታለች፤ይህ ቁጥርም ከአለም ሀገራት ሲነፃፀር በአንደኝነት ያስቀምጣታል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰአት 10,348 ዜጎቿን በኮሮና ቫይረስ ያጣችው ስፔን በሟች ቁጥር ሁለተኛ ነች፡፡

ቫይረሱ በደማችው የተገኘባቸው ቁጥር ከ1 ሚልዮን መሻገሩን ተከትሎ የአውስትራሊያው ዋና የህክምና ኦፊሰር ቁጥሩ ከዚህ በላይ ከፍ በማለት 5 ሚልዮን ሊደርስ ይችላል ብለዋል፡፡

የተለያዩ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ክትባት ምርምር እያደረጉ እንደሆነ የታወቃል፡፡

አዉሎ ሚድያ መጋቢት 25/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ