የእስራኤል የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በኮሮናቫይረስ እንደተያዙ ተረጋገጠ

0
103

ሚኒስትሩ አኮቭ ሊትዝማን እና ባለቤታቸው በተደረገላቸው ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን ነው የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር ያስታወቀው።

ጥንዶቹ ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውም ተነግሯል።

የ71 ዓመቱ የጤና ሚንስትር በእስራኤል ከፍተኛው በኮሮናቫይረስ የተያዘ ባለስልጣን ሆነዋል።

ቀደም ሲል የጠቅላይ ሚንስትር ኔታኒያሁ፤ የቅርብ አማካሪያቸው በቫይረሱ መያዙን ተከትሎ በተደረገላቸው ምርመራ ቫይረሱ እንደሌለባቸው መረጋገጡ ይታወሳል።

በእስራኤል ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከእነዚህም 26ቱ ህይወታቸውን አጥተዋል።

አዉሎ ሚድያ መጋቢት 24/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ