አለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል የሽብር ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዋልኩኝ አለ

0
98

አለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ በሽብር ተግባር የተሰማሩ በርካታ ሽብርተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

ተቋሙ ለስምንት ተከታታየ ቀናት በቆየው በዚሁ ዘመቻ በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሃገራት ድንበሮችና በአውሮፕላን ማረፊያዎች ሶስት ሚሊዮን የሚጠጉ ፍተሻዎችን ካደረገ በኋላ ነው፡፡

በዴሞክራቲክ ሪብሊክ ኮንጎ በኢንተርፖል የሚፈለጉ አምስት ሰዎች የተያዙ ሲሆን አንደኛው በአውሮፓ በተደራጀ ከባድ ወንጀል ሲፈለግ ነበር ተብሏል፡፡

በኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎችም የዘመቻው አካል እንደነበሩ ያሳወቀው ተቋሙ፤ከ80 ሚሊየን የሚበልጡ የጉዞ ሰነዶችን በያዘ የመረጃ ቋት አማካይነት ሃሰተኛ የጉዞ ሰነዶች ተጠቅመው የሚዘዋወሩ የሽብር ቡድን አባላት ላይ ክትትል ስለመደረጉም አንስቷል፡፡

የምስራቅ አፍሪካው ጽንፈኛ አሸባሪ ቡድን አል-ሸባብ እና በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጫካዎች መሽጎ ራሱን የተባበሩት ዴሞክራቲክ ኃይሎች በሚል የሚጠራውን ቡድን ያካተተ ዘመቻ መካሄዱን ቢቢሲ ተቋሙን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

አዉሎ ሚድያ መጋቢት 24/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ