ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ሕዝቡን አስጠነቀቁ

0
190

ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለው ቀውስ ከመሻሻሉ በፊት የከፋ ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደሚችል ብሪታኒያ ውስጥ ላሉ ቤተሰቦች በላኩት ደብዳቤ ላይ አስጠነቀቁ።

በኮቪድ-19 መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ እራሳቸውን ለይተው የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አስፈላጊ ከሆነ ጥብቅ የሆኑ ክልከላዎች ተግባራዊ እንደሚሆኑም ገልጸዋል።

የአገሪቱ ዜጎች ከቤታቸው ውጪ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ሊከተሏቸው የሚገቡ ደንቦችና የጤና መረጃዎችን ያየዙ በራሪ ወረቀቶች እንዲሰጧቸው ተነግሯል።

ይህም የሚደረገው መንግሥት ዜጎች ማድረግ ስለሚገቧቸው ነገሮች ግልጽ የሆነ መምሪያ አልሰጠም በሚል ከተተቸ በኋላ ነው።

ለ30 ሚሊዮን ቤተሰቦች እየተሰራጨ ያለውና 5.8 ሚሊዮን ፓዉንድ ወጪ ወጥቶበታል በተባለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ላይ “ከመጀመሪያው ትክክለኛውን እርምጃ በትክክለኛው ሰዓት ለመውሰድ ሞክረናል።

“ከሳይንስና ከህክምናው ዘርፍ የሚሰጡ ምክሮች ከዚህም በላይ የምንወሰድው እርምጃ እንዳለ ካመለከቱ ከማድረግ ወደ ኋላ አንልም” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ጆንሰን በደብዳቤያቸው ላይ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም “ግልጽ ላደርግላችሁ የምፈልገው ነገር፤ ከበሽታው ጋር በተያያዘ ያለው ሁኔታ ከመሻሻሉ በፊት የከፉ ሁኔታዎች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ እናውቃለን” ብለዋል በደብዳቤያቸው።

“ነገር ግን ዝግጅቶችን እያደረግን ሲሆን፤ ሁላችንም የተሰጠንን መመሪያ መከተል ከቻልን በበሽታው የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር ጥቂት ይሆናል። በቅርቡም ህይወት ወደ መደበኛ መስመሯ ትመለሳለች።”

ባለሙያዎች እንደሚሰጉት ከሆነ አሁን እየተወሰዱ ያሉት የእንቅስቃሴ እገዳ እርምጃዎችና አካላዊ እርቀትን የመጠበቅ ምክሮች ተግባራዊ ሆነው ውጤታቸው እስኪታይ ድረስ በሚኖሩት ሁለትና ሦስት ሳምንታት ውስጥ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር መጨመሩ አይቀርም።

በታላቋ ብሪታኒያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1,019 የደረሰ ሲሆን ትናንት ብቻ 260 ሰዎች ሞተዋል።

በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ 17,089 በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ይገኛሉ።

አዉሎ ሚድያ መጋቢት 21/2102 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ