የአማራ ክልል ባለፉት ሶስት ሳምንታት ከውጭ ሀገራት ወደ ክልሉ የተመለሱ ዜጎች በየአካባቢያቸው ለሚገኙ የመንግስት የጤና ተቋማት ሪፓርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ሰጠ

0
183

በአማራ ክልል የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል እና መቆጣጠር የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫውም ባለፉት ሶስት ሳምንታት ከውጭ ሀገራት ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ እና በአማራ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በአስቸኳይ በየአካባቢያቸሁ ወደሚገኝ የመንግስት የጤና ተቋም ሪፖርት እንዲያደርጉ እና ራሳቸውን እና ያገኟቸውንም ሠዎች ራሣቸውን እንዲያቀርቡ አሳስቧል።

ለክልሉ የገጠር ነዋሪዎች በሙሉ ያጋጠመን ችግር አስቸጋሪ መሆኑን በመረዳት ለግብይትም ሆነ ለሌላ ማህበራዊ ጉዳዮች ወደ ከተማ የሚያደርጉትን ጉዞ በማቆም ባሉበት ሆነው ራሳቸውን እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

የክልሉ ነዋሪዎች አሁን ካለው የወረርሽኙ አሣሣቢ ሁኔታ አንፃር እንደ አስፈላጊነቱ ታይቶ በክልሉ ውስጥ የሚደረግ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቆም ትዕዛዝ ሊሠጥ ሥለሚችል ይኸንኑ አስቀድማችሁ በማወቅ ወደ ቋሚ የመኖሪያ (መቆያ) ቦታችሁ ላይ በመሆን ከመንግስት የሚሠጠውን ትዕዛዝ በትኩረት እንድትጠባበቁ ኮሚቴው ማሳሰቡን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል ሲል ኤፍቢሲ ዘገቧል።

አዉሎ ሚድያ መጋቢት 21/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ