የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል 561 ታራሚዎች ከቃሊቲ ዛሬ ተፈቱ

0
67

ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በይቅርታ እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው መካከል 561 ታራሚዎች ዛሬ ተፈቱ።

ትናንት የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ሲባል 4 ሺህ 11 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን ተከትሎ የህግ ታራሚዎች እየተፈቱ ይገኛሉ።

በዚሁ መሰረት በዛሬው ዕለት ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብቻ 561 የህግ ታራሚዎች መፈታታቸውን የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች  አስታውቋል።

ዛሬ ከተፈቱት ውስጥ 20 ነፍሰ ጡሮችና ከህጻናት ጋር የታሰሩ እናቶች የሚገኙበት ሲሆን በአጠቃላይ ከተፈቱት መካከል 161 ሴቶች ናቸው።

አውሎ ሚድያ መጋቢት 17/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ