የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ሰልጣኞች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ሲባል ወደ ቤተሰቦቻቸው ተሸኙ

0
120

የአለም ወረርሽኝ በሆነው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት መንግስት ቅደመ መከላከል ለማድረግ በዩንቨርስቲ የሚገኙ ተማሪዎች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ አቅጣጫ መቀመጡ ይታወቃል ።

 ይህንንም ተከትሎ የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል እንደ ተቋም መንግስት የሰጠውን አቅጣጫ በመከተል የማዕከሉን ሰልጣኞች ወደ መጡበት አካባቢ እንዲሸኙ ተደርጓል ።

ሠልጣኞቹ ወደ መጡበት ዞን ከተማ ድረስ ትራንስፖርት የተዘጋጀላቸው ሲሆን በጉዞ ላይ ንክኪ እንዳይኖር የእጅ ጓንት ለሁሉም ሰልጣኞች እንዲሰጥ ተደርጓል ።

በተጨማሪ የማዕከሉን የጤና ባለሞያዎች በየጉዞ መስመሩ አብረው ድጋፍ እንዲሰጡ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።

አዉሎ ሚድያ መጋቢት 17/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ