ኬኒያ ዝቀተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ከገቢ ግብር ሙሉ በሙሉ ነጻ አድርገያለሁ አለች

0
90

ውሳኔው የተላለፈው የኮሮና ቫይረስ እያስከተለ ያለውን ሁሉን አቀፍ ተጽዕኖ ለመቀነስ ነው ተብሏል፡፡

አሁን አገሪቷ ያደረገችው የግብር ቅነሳ ፕሬዚደንት ኡሁሩ በኬኒያ ግብርን ለመቀነስ ከሚያካሂዱት እንቅስቃሴ መካከል መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

ኡሁሩ ባቀረቡት የግብር ቅነሳ መሰረት ወርሐዊ ገቢያቸው እስከ 24 ሺ የኬኒያ ሽልንግ የሆነ ኬኒያውያን ከግብር ሙሉ በሙሉ ነጻ ተደርገዋል፡፡

በተጨማሪም አገሪቱ በገቢ መጠን ይከፈል የነበረውን ግብር ከ30 በመቶ ወደ 25 በመቶ ስትቀንስ፣ የኗሪነትን ግብር ደግሞ እንዲሁ ከ30 ወደ 25 በመቶ ዝቅ አድርጋለች፡፡

በሸቀጥ ላይ የሚጣል ቀረጥ ደግሞ አሁን ካለበት 3 በመቶ ወደ አንድ በመቶ መቀነሱ ነው የተነገረው፡፡

ይህም በዋናነት ኮሮና በሚያስከትለው ኢኮኖሚያዊ ችግር ሊጎዱ የሚችሉ አነስተኛና መካለከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ለመደገፍ ነው ተብሏል፡፡

ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ የተጨማሪ እሴት ታክስን ከነበረበት 16 በመቶ ወደ 14 በመቶ እንደሚቀንስ የኬኒያ መንግሥት አስታውቋል፡፡

የግብር ቅነሳው ይፋ የሆነው ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬኒያታ በአገሪቱ ምክር ቤት ቀርበው የኮሮና ቫይረስን ለመግታት መደረግ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ሀሳብ ባቀረቡበት ወቅት መሆኑን ያስነበበው የኬኒያው ካፒታል ኤፍ ኤም ነው፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 17/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ