በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ምክንያት የኢንዱስትሪዎች ምርት ተቀዛቅዟል ተባለ

0
73

የዓለም ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ በቦሌ ለሚ ጨርቃጨርቅ እና ጋርመንትኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኙ የተለያዩ አምራች ኩባንያዎች ያላቸው የስራ እንቅስቃሴ ተቀዛቅዟል ተብሏል።

የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ትንሳኤ ይማም፤  ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የዓለም ስጋት መሆኑን ተከትሎ የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ይሁን እና ቫይረሱ በኢትዮጵያ በመከሰቱ በኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚገኙ የግል ባለሀብቶች ፍራቻ ያደረባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የግል ባለሀብቶቹ ባደረባቸው ስጋትም በምርት እንቅስቃሴው ላይ ከፍተኛ መቀዛቀዝ እየታየ ነው የሚሉት አቶ ትንሳኤ፤ አብዛኞቹ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን የሚልኩት ወደ አውሮፓና አሜሪካ በመሆኑና እነዚህ አገራት ደግሞ የዓለም ስጋት በሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት መዘጋታቸውን ተከትሎ ምርቶቹን መላክ አልተቻለም። በዚህም መቀዛቀዝ ይታይበታል ብለዋል፡፡

ኩባንያዎች የሚያመርቷቸው ምርቶች ወደ ገበያው እየደረሱ ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ገዥዎች ከዚህ ቀደም ያዘዙትን ትዕዛዝ እየሰረዙ መሆናቸውን ባለሀብቶቹ ገልፀዋል የሚሉት አቶ ትንሳኤ፤ ባለሀብቶቹ በቀጣይ ስላለው ሁኔታ የሚያውቁት ነገር ባለመኖሩ ለጊዜው የተቀበሉትን ትዕዛዝ ብቻ አምርተው እያስቀመጡ መሆኑን ተናግረው፤ በዚህ ምክንያትም ባለሀብቱ ላይ ፍራቻ መንገሱንና እንቅስቃሴው መቀዛቀዙን ገልፀዋል።

አዉሎ ሚድያ መጋቢት 17/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ