መንግስት ከአዲስ አበባ ወደ ክልሎች የሚደረግ ጉዞን ሊያስቆም ይገባል!!

0
68

አውሎ ሚዲያ ከትላንት ጀምሮ እንዳሰባሰበው መረጃ ከሆነ በአዲስ አበባ በፌዴራልና መስሪያቤቶችና በከተማ አስተዳደሩ ይሰሩ የነበሩ ሰራተኞች በቤት ውስጥ እንዲያሳልፉ መወሰኑን ተከትሎ በርካቶች ወደ ክልል እየወጡ ነው።

ቫይረሱ ለ14 ቀናት ምልክት ሳያሳይ የሚቆይ በመሆኑ ምርመራ ሳያደርጉ ወደ ክልል ከተሞችና ወደ አርሶ አደር ቤቶች በተለይ ወደ ወላጆቻቸውና ወደ ዘመዶቻቸው የሚደረገው ጉዞ ካልቆመ በሽታው በከፍተኛ ደረጃ እንዲስፋፋ በር ይከፍታል።

በመሆኑም ከአዲስ አበባ እየተነሱ ወደ ክልሎች የሚሔዱ ሰዎችን ማስቆም የግድ ይላል። ከተቻለም ከክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚደረገውን ጉዞም ማስቆም ቢቻል የቫይረሱን የመስፋፋት እድል ይቀንሳል።

አውሎ ሚዲያ በተለይም ከትላንት ጀምሮ በአዲስ አበባ የቫይረሱን መስፋፋት በመፍራት ወደ ክልሎች የሚሔዱ በርካታ መሆናቸውን የታዘበ ሲሆን እነዚህን ዜጎችን መንግስት ማስቆም አለበት በማለት ያሳስባል።

የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ የእያንዳንዱ ዜጋ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ጥንቃቄ አይለየን።

አዉሎ ሚድያ መጋቢት 16/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ