በለይቶ ማቆያ ማዕከላት ለሚቆዩና ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ ዜጎች መንግስት ሙሉ ወጪያቸውን ይሸፍናል-ኢንጂነር ታከለ ኡማ

0
97

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከኢትዮጵያ ውጭ የነበሩ ወገኖች በሚመለሱበት ጊዜ ወደ ህብረተሰቡ ከመቀላቀላቸው በፊት በለይቶ ማቆያ ማዕከላት በሚቆዩባቸው ጊዜዎች ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ ዜጎች ሙሉ ወጪያቸውን መንግስት እንደሚሸፍን መወሰኑን ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በፌስ ቡክ ገጻቸው አሳውቀዋል።

ኢንጂነር ታከለ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ መንግስት ከተለያዩ ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ መንገደኞች እና ወገኖች የለይቶ ማቆያ ማዕከል ማዘጋጀቱንም አስታውሰዋል።

በዚህ ወቅትም ለቆይታ ጊዜው ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ ዜጎች የከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ወጪያቸውን እንደሚሸፍን ተናግረዋል።

ኢንጂነር ታከለ አያይዘውም በመተሳሰብ ራስን መጠበቅ እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

አዉሎ ሚድያ መጋቢት 14/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ