በአዲስ አበባ ከተማ በተወሰኑ አካባቢዎች ለከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ማሻሻያ ስራ የኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል

0
93

 በዚሁ መሰረት፦ ዓርብ መጋቢት 11 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡ 00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ፣ Ø በአድዋ ድልድይ፣ በአቧሬ፣ በኳስ ሜዳ፣ በቤሌር፣ በእንደራሴ ሆቴል፣ በመለስ ፋውንዴሽን፣ በልቤ ፋና ኮንዶሚኒየም፣ በካዛንቺስ በከፊል፣ በሚኒሊክ ሆስፒታል፣ በስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ፣ በአራት ኪሎ፣ በፓርላማ፣ በግቢ ገብርኤል፣ ከካዛንቺስ እስከ ዮርዳኖስ ሆቴል፣ በጉድ ሼበርድ፣ በጣልያን ኤምባሲ፣ በቤላ ሆስፒታል፣ በቤተ መንግስት በከፊል፣ በግብፅ ኤምባሲ፣ በየካቲት ሆስፒታል፣ በቅድስተ ማርያም ቤ/ክ ጀርባ፣ በእሪ በከንቱ፣ በፒያሳ፣ በቀይ ባህር ኮንዶሚኒየም፣ በተፈሪ መኮንን ጀርባ፣ በአፍንጮ በር፣ በናይጄሪያ ኤምባሲ፣ በችሎት፣ በጉቶ ሜዳ እና በአካባቢዎቻው፣ ቅዳሜ መጋቢት 12 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 7፡00 ድርስ፣ Ø በጉርድ ሾላ፣ በቴሌ፣ በዶክተሮች ሰፈር፣ በፀሀይ ሪልእስቴት፣ በአምባሳደር ሪልእስቴት እና በአካባቢዎቻው፣ እንዲሁም በተመሳሳይ ቀን ቅዳሜ መጋቢት 12 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ስዓት ድረስ፣ Ø በፈረንሳይ ኤምባሲ፣ በጉራራ፣ በፊልም ማዕከል፣ በራስ ካሳ ክሊኒክ፣ በአቦ ቤተክረስቲያን፣ በእንጦጦ ኪዳነምህረት ቤ/ክ እና አካባቢዎቻቸው፣ እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ድርስ፣ Ø በለገሀር፣ በቴሌ ባር፣ በራስ ሆቴል፣ በአባሳደር፣ በሸራተን፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኮሜርስ፣ በፋና፣ በፖስታ ቤት፣ በጥቁር አንበሳ እና አካባቢዎቻቸው፣ በተመሳሳይ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ስዓት ድረስ፣በላምበረት፣ በመነሃርያ፣ በማደያ እና አካባቢዎቻቸው፣ በተጨማሪም በዚሁ ቀን ዕሁድ መጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ስዓት ድረስ፣  በሚኒሊክ ሆስፒታል፣ በስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ፣ በአራት ኪሎ፣ በፓርላማ፣ በግቢ ገብርኤል፣ ከካዛንቺስ እስከ ዮርዳኖስ ሆቴል፣ በጉድ ሼበርድ፣ በጣልያን ኤምባሲ፣ በቤላ ሆስፒታል፣ በቤተ መንግስት በከፊል እና አካባቢዎቻቸው፣ ስለሆነም ከላይ በተገለጹት አካበቢዎች በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት የኃይል አቅርቦት ስለሚቋረጥ ነዋሪዎች እና ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳስቧል።

አዉሎ ሚድያ መጋቢት 10/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ