ኬንያ በአባይ ግድብ ዙርያ የግብፅን ሃሳብ እንደምትደግፍ የግበጹ አህራም ኦንላይን ዘገበ

0
301

ትላንትና የኬናው ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ከግብጽ ፕሬዚደንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በስልክ ባደረጉት ቆይታ ነው ይህን ያሉት፡፡ ፕሬዚደንት እሁሩ ኬንያታ ብስልክ ቆይታቸው ኬንያ ግብጽ በአባይ ግድብ ጉዳይ ያላት አወንታዊ አቋም ትደግፋለች ከግብጽ ጎንም ትቆማለች ነው ያሉት፡፡

የግብጽ ፕሬዚደንት ቃል አቀባይ ባሳም ራድይ እንዳሉት ሁለቱም ፐሬዚዳንቶች በአሜሪካ አደራዳሪነት በኢትዮጵያ፣ በግብፅ እነዲሁም በሱዳን ሲደረግ ነበሩት ድርድሮች ከተቋረጠ ቡሃላ ሰላለው የአባይ ግድብ ሁኔታ ተነጋግረዋል ነው ያሉት፡፡

እሁሩ ኬንያታ በበኩላቸው  በአባይ ግድብ ዙርያ የግብፅ አቋም ቅን የፖለቲካ ፍላጎት ነው ሲሉ አሞካሽተውታል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፈው በአሜሪካ በነበረው የመጨረሻ ድርድር አለመገኘትዋ ያስታወሰው አህራም ኦንላይን ፣ ተጨማሪ ድርድሮች እና ንግግሮች እንደሚያስፈልጉም ጦቁሟል፡፡

በአሜሪካ የቀረበው የውሃ ሙሌትና አለቃቀቅ ምክረ ሃሳብ ከግብፅ በስተቀር ሱዳን እና ኢትዮጵያ አንፈርምም ማለታቸውም ይታወሳል፡፡

ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ግብፅ ሃሳቡዋ የሚደገፉ ሃገራትን ፍለጋ የተለያዩ የዲፐሎማሲ ስራዎችን እየሰራች ትገኛለች፡፡ ለዚህ ማሳያም የተለያዩ ዲፕሎማቶቿ ወደ አውሮፓ ህብረት፣ ሳኡዲ ፣ፈረንሳይ መላክዋ ይታወቃል፡፡

የግብፅ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሳሜህ ሹክሪ በዚህ ሳምንት በአባይ ግድብ  ዙረያ የአፍሪካ ሀገራት ድጋፍ ለማግኘት ወደተለያዩ የአፍሪካት ሀገራት ጉብኝት ጀምረዋል፡፡

በሳሜህ ሹክሪ ጉብኝት ብሩንዲ፣ደቡብ አፍሪካ፣ ታነዛንያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ፣ እንዲሁም ደቡብ ሱዳን ተካተውበታል ፡፡

የኢፌድሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባለፈው ሳምንት ከኬንያ መሪዎች ጋር  በአባይ ግድብ ዙርያ ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

አዉሎ ሚድያ መጋቢት 09/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ