ተጓዥ መንገደኞች ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄ ( የትራንስፖርት ሚኒስቴር መልእክት)

0
151

• በተሸከርካሪዎች ውስጥ በእጅ አለመጨባበጥ፣

• በቫይረሱ የተያዘ ሰው ወይም ከተያዙ ሰዎች ጋር ግንኙት ያለው ወይም የነበረው በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ዕራሱን በመገደብ አለመጠቀም ወይም የሚጠቀም ከሆነ የአፍና የአፍጫ መሸፈኛ ወይም ማስክ ማድረግ እና ሲያስነጥስ አፉን ሙሉ ለሙሉ በእጅ ክንዱ መከለል አለበት፣

• የጉንፋን እና የሳል በሽታ ያለበት ሰው በተቻለው መጠን ለመጓጓዝ በአውቶቡስ ባይጠቀም ወይም የሚጠቀም ከሆነ የአፍ መሸፈኛ ማስክ ማድረግ እና በተቻለ መጠን በመስኮት አጠገብ መቀመጥ/ እንዲቀመጥ ማድረግ፣

• አሽከርካሪዎችና ረዳቶች አውቶብሱ/ የተሸከርካሪው መስኮቶች ሳይከፈቱ ጉዞ አለመጀመር እና አለመጓጓዥ፣ ፍቃደኛ ያልሆነ ተጓጓዥ የበሽታውን አስከፊነት በማስረዳት እንዲከፈት ማድረግ፣ ፈቃደኛ ካልሆነ ከተሸከርካሪው መውረድ በዋናነት የሚደረጉ ዋና ዋና ጥንቃቄዎች መሆናቸውን ትራንስፖርት ሚኒስቴር ያስታውቃል።

አዉሎ ሚድያ መጋቢት 08/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ