ፓርቲዎች ሰነዶቻቸውን ግዴታ እስከ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ማሰገባት አለባቸው- ምርጫ ቦርድ

0
244

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለመመዝገብና ለምርጫ ለመወዳደር የሚፈልግ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የግለሰቦች ስብስቦች እንዲሁም ግንባርና/ቅንጅት መፍጠር የሚፈልጉ ፓርቲዎች፣ አስፈላጊ ሰነዶቻቸውን እስከ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለቦርዱ እንዲያስገቡ ጥሪ አቀረበ።

ቦርዱ ጥሪውን ያቀረበው የሚጠበቁበትን ተግባራት አከናውኖ ለመጪው ምርጫ ፓርቲዎችን ብቁ የማድረጉ ስራ ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ ነው ብሏል፡፡

ቦርዱ ባስተላለፈው ጥሪ መሠረት የካቲት 30 በኋላ የሚመጡ የምዝገባ ማመልከቻዎች በተለመደው አግባብ የሚስተናገዱ ቢሆንም፣ ያለው የአሠራር ሂደት ከሚወስደው ጊዜ አንጻር መጪው ብሔራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ የማይችሉ መሆኑን ገልጿል።

አዉሎ ሚድያ የካቲት 20/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ