የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ለብድር ብልሽት መዳረጉን ገለፀ

0
475

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በመንግስት ሓላፊዎች ጣልቃ ገብነት፤ በባንኩ ሰራተኞችና ሓላፊዎች በጥቅም መደለል ምክንያት ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ለብድር ብልሽት መዳረጉን ገለጸ፡፡

ባንኩ 86 ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ዕዳ ያለበት መሆኑን፣ 39 ቅርንጫፎቹን መዝጋቱንና 71 ተበዳሪዎቹ እንደጠፉበትም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ሀይለየሱስ በቀለ፤ ዛሬ የባንኩን የስድስት ወር የስራ አፈጻጸምና የአምስት ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ባንኩ ለ16 ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር የብድር ብልሽት የተዳረገው የመንግስት ስራ አስፈፃሚዎች ጣልቃ ገብነት፣ የባንኩ ሰራተኞችና ኃላፊዎች በጥቅም በመደለል በብድር መስጠታቸው ነው፡፡

እንዲሁም የፕሮጀክቶቹን የአዋጭነት ጥናት ሳይደረግና የተበዳሪዎቹ አቅም ሳይታወቅ ብድር እንዲሰጣቸው በመደረጉ ነው ብለዋል ሲል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል፡፡

አዉሎ ሚድያ የካቲት 20/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ