በአዲሱ ኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ መሠረት በአሮጌ እና አዲስ መኪና መካከል ያለው ልዩነት የገቢዎች ሚንሰቴር ይፋ አደረገ

0
13934

በአዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ጋር ተያይዞ ብዙ የፊስቡክ ገፃችን ተከታታዮች ደጋግማችሁ በአሮጌ እና አዲስ መኪና ላይ የተጣለው የኤክሳይዝ ታክስ ልዩነት እንድናቀርብ በጠያቃችሁት መሠረት የተወሰኑት ከታች በሠንጠረዥ ውስጥ ተዘርዝሯል፡፡

ይህም ከዚህ በፊት እንደተገለፀው መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች በብዛት የሚጠቀሙት ከ1 ሺህ 300 ሲሲ ያልበለጠ የፈረስ ጉልበት ያላቸው ተሽካረካሪዎች እና ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ኤክሳይዝ ታክስ አዲስ በሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ፣ ሙሉ በሙሉ ተበትነው የቀረቡ፣ በሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ እንዲገጣጠሙ በከፊል ተበትነው የገቡ እና አዲስ ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው የቀረቡ ላይ እንዲጣል የሚጠይቀው የኤክሳይዝ ታክስ ከ30 በመቶ ወደ 5 በመቶ ዝቅ እንዲል ማሻሻያ እንደተደረገበት አንስቷል።

በተጨማሪም ከ1 ዓመት እስከ ከ2 ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ እንዲጣል የሚጠይቀው የኤክሳይዝ ታክስ ከ80 በመቶ ወደ 55 በመቶ እንዲሁም፥ ከ2 ዓመት እስከ ከ4 ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ እንዲጣል የሚጠይቀው የኤክሳይዝ ታክስ ከ130 በመቶ ወደ 105 በመቶ ዝቅ እንዲል ማሻሻያ ተደርጎበታል።


ከ4 እስከ 7 ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ እንዲጣል የሚጠይቀው የኤክሳይዝ ታክስ ከ230 በመቶ ወደ 205 በመቶ ዝቅ እንዲል ማሻሻያ መደረጉ ተጠቅሷል።

ከ7 ዓመት በላይ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ እንዲጣል የሚጠይቀው የኤክሳይዝ ታክስ ከ430 በመቶ ወደ 405 በመቶ ዝቅ እንዲል ማሻሻያ መደረጉም ነው የተነሳው።

አዋጁ የካቲት 5 ቀን 2012 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀ ሲሆን ተግባራዊ መሆን የጀመረው ከየካቲት 6 ቀን ጀምሮ ነው፡፡
-ስለሆነም የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን ምርቶች የሚያመርት ድርጅት ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ በአዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ መሰረት ታክስ መሰብሰብ ያለበት መሆኑ፣
-አምራች ድርጅቶች በሚያከናውኑት ሽያጭ ላይ ኤክሳይዝ ታክስ ለመሰብሰብ ቀድም ሲል ባሳተሙት የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ የእጅ በእጅ ደረሰኝ ላይ የኤክሳይዝ ታክሱን በማስገባት እንዲሰበስቡ በጊዜያዊነት የተፈቀደ ሲሆን (እስከ የካቲት 30/2012) በዚሁ አግባብ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ፣
-በእጅ ላይ በሚገኝ ደረሰኝ ከመጠቀም ጎን ለጎን በታክስ ማዕከላት በመቅረብ በአዲሱ የኤክሳይ አዋጅ መሰረት ደረሰኝ ማሳተም እንደሚገባ፣
-አዋጁ ከጸደቀበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 6 ወራት ውስጥ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ምርቶችን የሚያመርቱ ድርጅቶች በሙሉ አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት መመዝገብ የሚያስፈልግ ሲሆን ከታክስ ባለስልጣኑ ፍቃድ ሳይሰጥ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን ምርቶች ማምረትም ሆነ ማከፋፈል የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትል ሲሆን፡-

ከላይ የቀረቡትን ጨምሮ በአዋጁ አተጋባበር ላይ አጠቃላይ መረጃ ለማግኘት ሳሪስ ሙለጌ ህንጻ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 421 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0118-931709 ወይም በኢ-ሜል አድራሻ exciseteam9@gmail.com መረጃና ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡


አዉሎ ሚድያ የካቲት 19/2012 ዓ.ም

1 COMMENT

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ