የአማራና የትግራይ ክልሎች የሁለቱን ሕዝቦች ግንኙነት ለማጠናከር ምሁራን ‘ፖለቲካዊና ህጋዊ መሰረት ያላቸው ችግሮችን መፍታት ይጠበቅባቸዋል ተባለ

0
96

በሠላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት የተዘጋጀውና እስከ ነገ የሚቀጥለው መድረክ የሁለቱን ሕዝቦች አንድነትና ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።

ውይይቱ ለሁለተኛ ዙር እየተካሄደ ያለ ሲሆን ለሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች ዘላቂ ሠላም እሴት ግንባታ ምሁራን የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ለማስቻል መዘጋጀቱም ተገልጿል።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሠላም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አልማዝ መኮንን ምሁራኑን የሠላም እሴት ግንባታው ሕዝባዊ መሰረት እንዲኖረው ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ልምድና እውቀታቸውን በመጠቀም ችግሮች በሳይንሳዊ መንገድ እንዲፈቱና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ እንዲጎለብት የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ በሁለቱ ክልሎች ሕዝቦች መካከል ለተፈጠረው የግንኙነት መሻከር መንስኤዎችን ለመለየት ጥናት ቢያስፈንግም ‘ፖለቲካዊና ህጋዊ መሰረት ያላቸው ችግሮች’ የሚሉት በትኩረት ይቃኛሉ ተብሏል።

በመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም ላይ የተስተዋሉ እንዲሁም ታሪካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ባሕላዊና ኢኮኖሚያዊ መሰረት ያላቸው ችግሮችም ይዳሰሳሉ።

በሠላም ግንባታው የሚሳተፉ ምሁራን እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን መጠንና ስፋት በውል በማጤንና በመመርመር የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የማመላከት ሚና መወጣት እንዳለባቸውም ተገልጿል።

ማኅበረሰቡ በተሞክሮ ያጎለበታቸው፤ በጊዜ የተፈተኑና ለችግሮች መፍትሄ የሚሆኑ ባሕላዊ የችግር አፈታት ዘይቤዎች በጥናትና ምርምር ጎልብተው ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግም እንዲሁ።

በሕዝቦች መካከል የጋራ ተጠቃሚነትን ለሚያጠናክሩ ፕሮጀክቶችና የልማት ስራዎች ትኩረት በመስጠት ማገዝ እንደሚጠበቅባቸውም ተነግሯል።

ከምሁራኑ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ ይበልጥ ተጠናክሮ የሚቀጥልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይጠበቃልም ተብሏል።

አዉሎ ሚድያ የካቲት 17/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ