በጊንጪ ከተማ የፖሊስ ካምፕ ላይ የቦንብ ጥቃት ደረሰ

0
117

በትናንትናው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ጊንጪ ከተማ በሚገኝ የፖሊስ ካምፕ ላይ የቦንብ ጥቃት ደርሷል፡፡

በከተማው ትናንት ከምሽቱ 2 ሰዓት በደረሰው በዚህ ጥቃት በወቅቱ በስራ ላይ በነበሩ ሁለት የፖሊ አባላት ላይ በጭስ የመታፈን መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ በቀር የከፋ አደጋ አለመድረሱን የክልሉ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ተናግረዋል፡፡

ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠሩ ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አቶ ጌታቸው  ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡

በጥቃቱ ተሳትፈዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ማንነት እስካሁን በተደረገው ምርመራ አለመታወቁን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ከትናንት በስቲያም በአምቦ ከተማ በተካሄደ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት በ29 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን ይታወሳል  ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው።

አዉሎ ሚድያ የካቲት 17/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ