በኬብል ስርቆት ምክንያት ከጊዮርጊስ እስከ መሿለኪያ ያለው የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ተቋረጠ

0
133

ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ከ1ነጥበ 6 ሚሊዮን ብር በላይ የኬብል ስርቆት ተፈጽሟል።

የጥገና ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ታመነ ሽመልስ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ባለፈው አራት ቀን ከልደታ እስከ ስታዲየም ባለው የባቡር መስመር የሲግናል ኮሙኒኬሽን ኬብል ተቆራርጦ ተገኝቷል።

ከዚህ ቀደም የመብረቅ መከላከያ፣ ለኮሙኒኬሽንና ለሌሎች ተግባራት የሚውሉ ገመዶች ስርቆት በተደጋጋሚ ተፈጽሟል።

”በዚህም ሳቢያ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ በሆኑ ባቡሮች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት አልተቻለም ነው” ያሉት።

ከዚህ ጋር በተያያዘም በሲኤምሲ እና በሌሎች መስመሮች የትራንስፖርት ስምሪት መስተጓጎል ማጋጠሙን አቶ ታመነ አብራርተዋል።

”ይህንን ለፖሊስ አካላት ብናሳውቅም ችግሩን ግን በቀላሉ መፍታት አልተቻለም” ብለዋል።

”በቅርቡ የተፈጸመው ድርጊት ግን ሆን ተብሎ የተደረገ የሚመስል ነው” ያሉት አቶ ታመነ ህገ-ወጦችን ለመከላከል በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

በዚህም ሳቢያ ከትናንት ጀምሮ ያለው የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡንና በቅርቡ ስራ ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በአሁኑ ጊዜ ህብረተሰቡ የሚያገኘውን አገልግሎት ከማስተጓጎሉም ባለፈ ተቋሙ በቀን ከ100 ሺህ ብር በላይ እያጣ መሆኑን ተናግረዋል።

አዉሎ ሚድያ የካቲት 17/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ