የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ በክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ያተኩራል ተባለ

0
79

ዛሬ የሚጀምረው የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ በህግ የበላይነትና የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ላይ በትኩረት እንደሚመክር ተገለጸ።

የጨፌው አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ጨፌው ባካሄደው 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ለጸጥታ ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደነበር በማስታወስ፥ ይህንንም ተከትሎ በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች ሰላማዊ ሁኔታ እንዳለ ተናግረዋል።

ሆኖም አሁንም ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ ጨፌው ይሰራል ብለዋል።

በሌላ በኩል በክልሉ የተከናወኑ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ባሉት ቋሚ ኮሚቴዎች ሲገመገም እንደነበር አንስተዋል።

በዚህም የአስፈጻሚ አካላት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ታይቶ ግብረ መልስም ተሰጥቷል።

ጨፌው የተሰጠው ሀላፊነት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማጠናከር እንደመሆኑም ከአጎራባች ክልል ህዝቦች ጋር በቅርበት ተሰርቷልም ነው ያሉት።

ዛሬ በሚጀምረው ጉባኤ የስድስት ወራት የክልሉ መንግስት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች እና ሹመቶችም ቀርበው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ ይፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዘገባው የኤፍቢሲ ነው

አዉሎ ሚድያ የካቲት 10/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ