በኢትዮጵያ በኮሌራ ወረርሽኝ የ76 ሰዎች ሕይወት አለፈ

0
232

በኢትዮጵያ በተከሰተው የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ እስካሁን የ76 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ በሽታው በአሁኑ ወቅትም በኦሮሚያ፣ በደቡብ እና በሱማሌ ክልሎች በወረርሽኝ መልክ እየተሰራጨ ነው ብሏል።

ይህ በሽታ “ቫይብሮ ኮሌራ” በተባለ ተህዋስ አማካኝነት የሚከሰትና አንጀትን የሚያጠቃ ነው።

ኮሌራ በተህዋሱ በተበከለ ምግብና ውሃ አማካኝነት የሚመጣ ሲሆን አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ምልክቶቹ እንደሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

የሰውነትን ፈሳሽ በመጨረስ አቅም እንደሚያሳጣና ሕክምና ካላገኘ ምልክት ማሳየት በጀመረ በአምስት ቀናት ውስጥ ለሞት ሊዳርግ እንደሚችልም ይናገራሉ።

የኮሌራ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ አብዛኞቹ አካባቢዎች እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከሚያዚያ 2019 ጀምሮ መከሰቱ ይታወቃል።

ወረርሽኙ ተከስቶባቸው ከነበሩ አካባቢዎች መካከል አዲስ አበባን ጨምሮ አማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር እና ሱማሌ ክልሎች ይጠቀሳሉ።

ይሁንና በኦሮሚያ፣ ደቡብ እና ሱማሌ ክልሎች አሁንም በሽታው በወረርሽኝ መልክ ተሰራጭቶ እንደሚገኝና በበሽታው የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርም እየጨመረ መሆኑን ተናግረዋል።

ወረርሽኙ በአሁኑ ወቅት በደቡብ ክልል በ11፣ በኦሮሚያ በሦስት፣ እንዲሁም በሶማሌ ክልል በሁለት ወረዳዎች በድምሩ በ16 ወረዳዎች እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ዘገባው የኢዜአ ነው

አዉሎ ሚድያ የካቲት 05/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ