33ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ይጠናቀቃል

0
153

ለሁለት ቀናት ”የመሳሪያ ድምጽ የማይሰማባትን አህጉር እንመስርት” በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ የሚገኘው 33ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ይጠናቀቃል።

በዚህ የ33ኛው የመሪዎች ጉባኤ 32 የህብረቱ አባል አገራት ፕሬዝዳንቶች፣ 3 ምክትል ፕሬዝደንቶች፣ 7 ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ ሌሎች በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ የተመራ ልኡክ እንደሁም የህብረቱ አባል ያልሆኑ 3 ጠቅላይ ሚኒስትሮች ተሳትፈዋል።

ከተመድ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ ጨምሮ 3 የስራ ሃላፊዎች ተገኘተዋል።  በተጨማሪም የህብረቱ አባል አገራት 18 ቀዳማዊ እመቤቶች ከህብረቱ ጉባኤ ጎን ለጎን በሚደረጉ የተለያዩ ስብሰባዎች በመሳተፍ ለይ የሚገኙ ሲሆን፤ ጉባኤው ዛሬ ከስዓት በኋላ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል ሲል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡

አዉሎ ሚድያ የካቲት 02/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ