የበረሃ አምበጣ በሶማሊያ በአልሸባብ ቁጥጥር ስር በሆኑ አካባቢዎች እየተስፋፋ ነው

0
207

በአልሸባብ  ቁጥጥር ስር በሆነቸው  የሶማሊያ ፑንትላንድ ክልል  የበረሃ አምበጣ እየተስፋፋ መሆኑ ተገለጸ። ክልሉ በአልሸባብ የአሸባሪ ቡድን ቁጥጥር ስር በመሆኑም የአንበጣ ማጥፊያ መድሃኒት ለመርጨት አስቸጋሪ  እንደሆነ ነው የተገለጸው ።

በስፍራው መድሃኒቱን መርጨት ካልተቻለም የአንበጣውን ስርጭት ለመቆጣጠር አመታት ሊፈጅ እንደሚችል ተመልክቷል።

የአለም የምግብና የእርሻ ደርጅት (ፋኦ) የበረሃ አምበጣውን ስርጭት ለመቆጣጠር   የአለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች 76 ሚሊዮን ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ቢጠይቅም  እስካሁንም 19 ሚሊዮን ዶላር ሰብስብያለው ማለቱ ይታወሳል። የአለም የምግብና የእርሻ ደርጅት የበረሃ የአንበጣ መንጋ በ ኢትዮጵያ ፣ በኬንያ እና በሶማልያ ስርጭቱ አሳሳቢ ነው ብሏል፡፡

የበረሃ አንበጣ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ከ10 ሚሊዬን በላይ የሚደርሱ ሰዎችን ለከፋ የረሃብ ቀውስ ሊዳርግ እንደሚችል መረጃዎች ያመለክታሉ።

አዉሎ ሚድያ የካቲት 02/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ