የአቶ ዳውድ ኢብሳ፤ የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የአቶ ጃዋር መሀመድ ጠባቂ የነበሩት የመንግስት የጸጥታ አባላት ተነስተዋል

0
651

የኦነግ ሊቀ-መንበር የሆኑት የአቶ ደውድ ኢብሳ  ፤ የኢዜማ ፕሬዚዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ በቅርቡ ኦፌኮን የተቀላቀሉት አቶ ጃዋር መሃመድ በመንግስት ተመድበውላቸው የነበሩት ጥበቃዎች ተነስተዋል ተብሏል፡፡

እነዚህ ፖለቲከኞች ከውጭ ወደ ሃገር ከመጡ ጀምሮ በመንግስት ጥበቃ ተመድቦላቸው የነበረ ሲሆን አሁን ግን ጥበቃዎቻቸው ሙሉ በሙሉ መነሳታቸው ነው የተነገረው፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ከሃላፊነቴ ውጭ ለግለሰዎች ጥበቃ እንድመድብ እና ጥበቃ እንዳደርግ ተገድጄ ነበር ያለ ሲሆን አሁን ግን ጥበቃዎቹን ማንሳቱን አሳውቋል

አቶ ጃዋር መሀመድ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ጥበቃዎቹ ሊነሱብኝ ነው በሚል በፃፉት ፅሁፍ የተነሳ በኦሮሚያ እና አጎራባች ክልሎች በተቀሰቀሰ ተቃውሞ  86 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡

አሁን ላይ ጥበቃዎቻቸው የተነሱባቸው ፖለቲካኞች ማለትም አቶ ዳውድ ኢብሳ ፤ጃዋር መሀመድ እና ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ  ስለጥበቃዎቻቸው መነሳት ተነገረ እንጅ መንግስት ምን ሊያድርግ እንዳሰበ ግን የታወቀ ነገር የለም፡፡

በተለይም ከዚህ በኋላ ጥበቃ ይመደብላቸዋል ወይስ በግላቸው ይቀጥራሉ የሚለው በሂደት የሚታይ ነው፡፡

አዉሎ ሚድያ ጥር 29/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ