ከአዲስ አባባ ድሬዳዋ የሚሄደው ባቡር በተዳጋጋሚ እገታ እየደረሰበት ነው ተባለ፡፡

0
449

ከሰበታ ተነስቶ ድሬዳዋ -ጅቡቲ የሚደረገው የባባር ጉዞ በተዳጋጋሚ በሚደርስበት ዕገታ መንገደኞች እየተስተጓጎሉ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ባሳለፍነው ረቡዕ ጥር 27/2012 ዓም ከአዲስ አበባ ድሬደዋ -ጅቡቲ ታሳፈረው ጉዞ የጀመሩ ሰዎች  በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሀረርጌ ቦርደዴ ከተማ አካባቢ ባቡሩ በመታገቱ ለሰአታት ለመቆም ተገደው ነበር ተብሏል፡፡

በቦታው የነበሩ ተገልጋዮች ለአውሎ እንዳሳወቁት ከሆነ ባቡሩ ከመቆሚያ ጣቢያው ውጭ በድንገት የቆመ ሲሆን ከጥቂት ቆይታ በኋላ ባቡሩ ውስጥ በድምፅ “ባቡሩ በአካባቢው ነዋሪዎች ታግቷል። የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ከፖሊስ ጋር በመሆን ድርድር እያደረገ ስለሆነ ላልተወሰነ ሰዓት እንድትታገሱን እንጠይቃለን።” የሚል መልእክት እንደተነገራቸው ተናገረዋል፡፡

ይህም ሆኖ ባቡሩ ከእነ ተሳፋሪዎቹ የታገተበት ምክንያት ባይገለፅም 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ያክል ጉዞው መስተጓጎሉን ተናገረዋል፡፡

በጉዞው ላይ የታገተው ባቡር  14 ፉርጎ የነበረ ሲሆን አንድ ፉርጎ 118 ሰው የመያዝ አቅም ያለው ነው፡፡ ይህም ሆኖ ባቡሩ  ከመጫን አቅሙ በላይ ብዙ ሰው ተሳፍሮበት  ነበር ተብላል። ባቡሩ የታገተው ከ7:40 እስከ 9:55 ድረስ  ሲሆን ባባሩ ውስጥ የነበሩት አብዛኛው ተሳፋሪዎች የድሬዳዋና ጅግጅጋ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ነበሩ።

ባቡሩ ከእገታ ተለቆ ለተሳፋሪዎችም ከ እገታ እንደተለቀቁ በባሩ ውጥ በተዘረጋው የድምጽ ሲሰተም ተነገሯቸው ጉዞ መቀተሉን ነው በበባሩ ውስጥ የነበሩ ሰዎች የነገሩን፡፡

ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ስለ ጉዳዮ መከሰት ለማጣራት ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም ክስተቱ ግን በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ እያጋጠመ ነው ተብሏል፡፡

አዉሎ ሚድያ ጥር 29/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ