አብን በመንግሥት ድጋፍ በኦርቶዶክስ ኃይማኖት ተከታዮች ላይ ጥቃት እንዲደርስባቸው እየተቀሰቀሰ ነው ፤ ይህ ሊቆም ይገባል አለ

0
236

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ  (አብን) ባወጣው መግለጫ  ጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም ከሌሊቱ 7:00 በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል አካባቢ፣ 24 ቀበሌ አዲስ የተሰራውን መቃኞ ቤተክርስቲያን ለማፍረስ የሄዱ ፓሊሶች ቤተክርስቲያኑ በምሽት ሊፈርስ አይገባም ባሉ የእምነቱ ተከታዮች ላይ በተኮሱት ጥይት የደረሰው የሰው ሕይወት መጥፋት ተጠያቂው መንግስት ነው ብሏል፡፡

የአካባቢው የክርስትና እምነት ተከታይ ያለበትን የማምለኪያ ቦታ ችግር ከከንቲባ ድሪባ ኩማ ጊዜ ጀምሮ በሰላማዊ መንገድ ሲያቀርብ መቆየቱንና ለጥያቄው በጎ ምላሽ አለማግኘቱን አብን ከአካባቢው ሕዝብ ባሰባሰኩት መረጃ አረጋግጫለሁ  ሲል አብን  በመግለጫው አስፈረዋል፡፡

አብን አክሎም የተሰራው ቤተ-እምነት ጋር ችግር አለ ተብሎ ቢታሰብ እንኳ ሕጋዊ ሥርዓቱን በተከተለ አግባብ ሕዝቡን በማወያየት መፍታት ሲገባ፤ በውድቅት ሌሊት ሄዶ ኃይል በመጠቀምና የሰው ሕይወት በማጥፋት ሕግ ለማስከበር የተሄደበት መንገድ መንግሥት ለዜጎች ያለውን ግዴለሽነት በግልፅ ያሳየ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

ባለፉት ሁለት አመታት መንግሥት ባሳየው ቸልተኝነት የሁሉም ሃይማኖቶች ቤተ እምነቶች ተቃጥለዋል፤ የኃይማኖት አባቶች ከኢትዮጵያዊነት ባሕል ባፈነገጠ መልኩ ተገድለዋል፤ የእምነቱ ተከታዮች ለእስራት፣ ለእንግልትና ለሞት ተዳርገዋል።

 ከዚህ በተጨማሪ በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አንዳንድ ግለሰቦች በመንግስት ድጋፍ በኦርቶዶክስ ኃይማኖት ተከታዮች ላይ ጥቃት እንዲደርስባቸው ሲቀሰቅሱ እየታየ ነው፤ይህ ነገር በጊዜ ኃይ ሊባል እንደሚገባ አብን አሳስቧል፡፡

መንግሥት ለሰው ሕይወት መጥፋት ምክንያት የሆኑ አካላትን በሙሉ ለሕግ እንዲያቀርብና የፍርድ ሂደቱንም ለሕዝብ እንዲያሳውቅ ብሎም የአካባቢውን ሕዝበ ክርስቲያን የአምልኮ ቦታ ጥያቄም ከአካባቢው ማስተር ፕላን ተጣጥሞ በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ አብን ጠይቋል፡፡

 አውሎ ሚድያ   ጥር 28/2012 ዓም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ