22 ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ለሊት 7 ሰአት በተከሰተ ግጨት የሁለት ሰዎች ሂወት አለፈ

0
139

ዛሬ ምሽት  ከሌሊት 7:00 ጀምሮ 22 መንገድ፣ ቅዱስ ገብርኤልን ሆስፒታል አካባቢ አፍሮ ፅዮን ኮንስትራክሽን ጎን ካለው ክፍት ቦታ ላይ ለብዙ አመታት ክፍት የነበረ፣ ጎዳና ላይ ከማደር ባለፈ ልጆች የሚጸዳዱበት ቦታ ላይ ያለፈው እሁድ “ራዕይ ታይቶናል!” ብለው ከክፍለ ሀገር የመጡ ካህናት ታቦት ይዘው በመምጣት ዳስ ጥለው መከተማቸውን ተከትሎ የ22 እና የ24 ቀበሌ ወጣቶች፣ ትላልቅ ሰዎችም ጭምር ኾነው ቦታውን በጋራ በመጠበቅና በማጽዳት ቦታውን እስከ ትላንት ድረስ ጠብቀዋል።

የሚመለከተው አካል በቀን ላይ ምንም አይነት ቦታውን የማስለቀቅ ሥራ ሳይሰራ ሰኞ ለማክሰኞ ምሽት በሌሊት በመሄድ በአድማ በታኝ ለማስለቀቅ ጥረት በማድረጉ ህዝቡም በጋራ በመሆን ከአድማ በታኞች ጋር ተጋጭቷል።

ጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት እንዲያገኝም ሆኗል።ነገሩን ትኩረት ሰጥቶ በሰላም ቦታውን ለማስለቀቅ ህጋዊ በሆነ መልኩ ከመሞከር ይልቅ ዛሬ /ማክሰኞ ለረቡዕ አጥቢያ/ ሌሊት 7:00 ሰዓት ሲሆን አድማ በታኝ ሌሊት ኃይል በመጠቀም ለማስለቀቅ ከመሞከር ባለፈ አስለቃሽ ጭስ ሲጠብቁ በነበሩ እናቶች፣ ወጣቶች እና የእምነቱ ተከታይ የሆኑ ልጆችም ጭምር ላይ በመወርወር እና በመተኮስ ወደ ግጭት አምርተዋል ብለዋል የሰፈሩ ነዋሪዎች። 

 በተጨማሪም እስካሁን ሁለት ወጣቶች በጥይት ተመተው መሞታቸው የአካባቢ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የቦሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው አረንጓዴ ስፍራ ተብሎ የተተወ ስፍራ ላይ ፅላት ሳይገባበት ቤተ ክርስቲያን እንሰራለን በማለት ህግ ለማስከበር ሙከራ ሲደረግ የፖሊስ መኪና አቃጥለዋል ብለዋል።

አዉሎ ሚድያ ጥር 27/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ