የኬንያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ ህልፈተ ህይወትን ተከትሎ ኬንያ ብሄራዊ ሀዘን አወጀች

0
90

የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝደንት የነበሩት ሚስተር ዳንኤል አራፕ ሞይ ህልፈተ ህይወትን ተከትሎ ስርዓተ ቀብራቸው እስኪፈጸም ድረስ ብሄራዊ የሀዘን ቀን እንዲሆን መታወጁ ተገለጸ።

ኬንያ ለ24 አመት የመሯት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ በ95 ዓመታቸው አርፈዋል።

በጡረታ ክብር ላይ የነበሩት የቀድሞው ፕሬዝዳንት በናይሮቢ ሆስፒታል የህክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው ሳለ ህይወታቸው እንዳለፈ የተነገረ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ስርዓተ ቀብራቸው እስኪፈጸም ድረስ ብሄራዊ የሀዘን ቀን እንዲሆን የኬንያው ፕሬዝደንት አሁሩ ኬንያታ መልእክት ማስተላለፋቸው በመረጃው ተጠቅሷል።

ላለፉት 24 አመታት ያስተዳደሩት እኝሁ ፕሬዝደንት ለክብራቸው መግለጫ ይሆን ዘንድ በሁሉም አካባቢ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ኬንያታ ትዛዝ አስተላልፈዋል።

ፕሬዝዳንት አራፕ ሞይ ኬንያን ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን ካገኘች በኋላ ስልጣን የያዙ ሁለተኛው ፕሬዝዳንት ነበሩ።

የቀብር ስነስርዓታቸው በወታደራዊ ማርሻ በታጀበ ክብር እንደሚደረግላቸውም በመረጃው ሰፍሯል።

ዳንኤል አራፕ ሞይ እኤአ ከ1978 ጀምሮ የመጀመሪያው የኬንያ ፕሬዝዳንት ጀሞ ኬንያታ በሞት ከተለዩበት ዕለት አንስቶ ኬንያን በፕሬዝዳንትነት እንዳስተዳደሩ ቢቢሲ በዘገባው አውስቷል።

አዉሎ ሚድያ ጥር 26/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ