የኖቭል ኮሮና ቫይረስ በሽታ ለመደበቅ ባለስልጣናት ዶክተሮችን ያስፈራሩ ነበር ተባለ

0
453

በጥር ወር መጀመሪያ ላይ የኮሮናቫይረስ በዋናነት የተቀሰቀሰባት የዉሃን ከተማ ባለስልጣናት ስለበሽታው መከሰት የሚያመለክቱ መረጃዎችን ለመሸፋፈን ጥረት ሲያደርጉ ነበር።

የበሽታውን መከሰት በተመለከተ ለሰዎች በመንገር እንዲጠነቀቁ ሲመክር የነበረ አንድ ዶክትርን ፖሊሶች ቤቱ ድረስ መጥተው ከድርጊቱ እንዲቆጠብ አስጠንቅቀውት ነበር። ነገር ግን ከአንድ ወር በኋላ በሽታው በወረርሽኝ መልክ ተከስቶ ዓለምን ማስጨነቅ ሲጀምርና ሐኪሙ ምን ተብሎ እንደነበረ ሃኪም ቤት ተኝቶ ታሪኩን ይፋ ሲያደርግ ጀግና ተብሎ እየተወደሰ ነው።

“ጤና ይስጥልኝ፤ ሊ ዌንሊያንግ እባላለሁ፣ በዉሃን ማዕከላዊ ሆስፒታል የዓይን ሃኪም ነኝ” በማላት ይጀምራል የዶክተሩ መልዕክት።

ዶክተሩ ይፋ ያደረገው መልዕክት የኮሮናቫይረስ በተከሰተባቸው የመጀመሪያ ሳምንታት ዉሃን ውስጥ ያሉ ባለስልጣናት በሽታውን ለመሸፋፈን ያደረጉትን ጥረት ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው ተብሏል።

ታህሳስ ወር ላይ ወረርሽኙ በተከሰተበት ማዕከል ውስጥ ይሰራ የነበረው ዶክተር ሊ በአንድ እንግዳ ቫይረስ ተጠቅተው የመጡ ሰባት ሰዎችን አግኝቶ ነበር፤ እሱም በሽታው ከ15 ዓመታት በፊት ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ሆኖ የነበረው ‘ሳርስ’ ነው ብሎ ገምቶ ነር።

እነዚህ የበሽታው ክስተቶች ሁናን ተብሎ ከሚጠራው የባሕር ውስጥ ምግቦች መሸጫ ገበያ የተከሰተ እንደሆነ ስለታሰበ ህሙማኑ ከሌሎች ተለይተው በሆስፒታሉ ክትትልና ህክምና እንዲያገኙ ውስጥ ተደረገ።

እንደ አውሮፓዊያኑ ታህሳስ 30 ላይ ዶክተሩ በአንድ የቡድን መልዕክት መለዋወጫ መድረክ ላይ ለሙያ አጋሮቹ ዶክተሮች ስለወረርሽኙ መከሰትና እራሳቸውን ለመጠበቅ የመከላከያ አልባሳትን እንዲጠቀሙ የሚመክር መልዕክት አስተላልፎ ነበር።

በዚያ ወቅት ዶክትር ሊ ያላወቀው ነገር ቢኖር የወረርሽኙ ምክንያት የሆነው ተህዋስ በኋላ ላይ እንደተደረሰበት ፍጹም አዲስ አይነት የኮሮናቫይረስ እንደሆነ ነበር።

ቢቢሲ እንዳለው ከአራት ቀናት በኋላ ከሕዝብ ደህንንት ቢሮ ባለስልጣናት መጥተው አንድ ደብዳቤ ላይ እንዲፈርም ነገሩት። ወረቀቱም ዶክተሩን “ሐሰተኛ አስተያየቶችን በመስጠት” ይህም “በከፍተኛ ሁኔታ ማኅበራዊ ሥርዓትን የሚያናጋ” መሆኑን በመግለጽ ጥፋተኛ አድርጎ የሚከስ ነበር።

አዉሎ ሚድያ ጥር 26/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ