ከፌደራል መንግስት የተነሱ የህወሓት አባላትና ባለስልጣናት ብሔራዊ ባይቶና ዓባይ ትግራይ(ባይቶና) መነሳታቸው ኢሕገ-መንግስታዊ ነው አለ

0
153

በኢህአዴግ የውስጥ አለመስማማት ተከትሎ የትግራይ ተወላጆች ትኩረት ባደረገ መልኩ እየተደረገ ስላለው የከስልጣን ማንሳት እንዲሁም ዝቅ ብለው እንዲሰሩ ማድረግ ፍፁም ኢሕገ-መንግስታዊ አካሄድ ነው፣ለዚህም ፓርትያችን ባይቶና  አካሄዱን ይቃወማል ነው ያሉት በመግለጫው።

የባይቶና የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሀላፊ የሆኑት አቶ ክንፈ ገ/የውሀንሰ ባይቶና እንደፓርቲ ብልፅግና ፓርቲ ህገ ወጥ ፓርቲ ነው ብሎ ነው የሚያምነው ብሏል።አክለውም በትግራይ ላይ ግልፅ የጦርነት  ዘመቻ የሚያደርጉ ሰዎች ሹመት በመስጠት  የትግራይ ህዝብ በተደራጀ መልኩ ለመጉዳት እየሰራ ያለ ሀይልም ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በትግራይ ህዝብ ላይ የተጋረጠ አደጋ አለ ብለን እናምናለን ያሉት ደሞ የፓርቲው ውጪ ጉዳይ ሀላፊ የሆኑት አቶ ክብሮም በርሀ ናቸው። ብልፅግና ፓርቲ እየሄደበት ያለው ሁኔታም ሀገሪትዋ በህገ መንግስት ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ የሚያስረዳ ነው ነው ያሉት።

የትግራይ ተወላጆች የሆኑት የንግድ ማህበረሰቡ ላይም ጫና እየደረሰባቸው እንደሆነ ደርሰንበታል ይህም አጥብቀን እንቃወማለን ብሏል ፓርቲው በመግለጫው።

ብልፅግና ፓርቲ ሳይቀበሉ በትልቅ ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች አሉ ይሁን እንጂ የእነ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሄር እና ሌሎች መነሳት በብሄራቸው ምክንያት ነው ምንለውም ለዚህ ነው ብሏል ፓርቲው።

አዉሎ ሚድያ ጥር 25/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ