የኮሮና ቫይረስ ‘አለም አቀፍ የጤና ስጋት’ ተብሎ ታወጀ

0
533

የኮሮና ቫይረስ ‘አለም አቀፍ የጤና ስጋት’ ተብሎ መታወጁን የአለም ጤና ድርጅት ገለፀ ።

የአለም ጤና ድርጅት (WHO) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖም ትናንት በሰጡት መግለጫ ቫይረሱ በአለም አቀፍ በስጋትነት ደረጃ የታወጀው ቻይና ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሀገራት ጭምር በፍጥነት እየተስፋፋ በመሆኑ ነው ብለዋል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ቻይና በሽታውን ለመቆጣጠር እያደረገች ያለውን ሁሉን አቀፍ ምላሽ አድንቀዋል፡፡

እንደ አለም ጤና ድርጅት መግለጫ የኮሮና ቫይረስ አሁን ባለበት ሁኔታ ደካማ የጤና ስርዓት ባላቸው ሀገራት ከተሰራጨ እጅግ አሳሳቢ ይሆናል።

በመሆኑም ድርጅቱ የቫይረሱ መነሻ የሆነችው ቻይናን ጨምሮ ሌሎች ሀገራትም በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የአለም ጤና ድርጅት ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል ዳይሬክተር፡፡

በኮሮና ቫይረስ እስካሁን 213 ሰዎች የሞቱ ሲሆን የተጠቁ ሰዎች ቁጥርም ከ9,000 በላይ ደርሷል ተብሏል።

ቫይረሱ በአለም አቀፍ ደረጃ በ18 ሀገራት እንደተሰራጨ መታወቁን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

አዉሎ ሚድያ ጥር 22/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ