ጠቅላይ ሚንስትሩ ሚንስትሮችን ፓርላማ ሳያፀድቅ ይፋ ማድረጉ ስህተት ነው ተባለ

0
503

ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው የ5ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ጉባኤው የሶስት ሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ አፅድቋል፡፡ በዚህም መሰረት ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር፣ ኢ/ር) የትምህርት ሚኒስትር፣ አብርሃ በላይ (ዶ/ር) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እንዲሁም አቶ መላኩ አለበል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
ሹመቱን በማፅደቁ ሂደትም ጥር 6፣ 2012 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረቡት የእነዚህ ተሿሚዎች ሹመት ቀድሞ ይፋ መደረጉ በምክር ቤቱ አባላት ስህተት ነው ተብልዋል። የሚንስትሮቹ ሹመትም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚንስትሮች የማፅደቅ ስልጣን የሚጋፋ ነው የተባለው።
ምክር ቤቱ በተጨማሪም ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የተላኩለትን ሰባት ውሳኔዎች ላይ ተወያይቶ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴም መርቷል፡፡
በዚህ ጉዳይም የተለያዩ የፖለቲካ ተንታኞች ተሿሚዎቹ ቀድሞ ይፋ መደረጋቸው ያካሄድ ችግር ብቻ ሳይሆን የቀጣይ የምንግስት አካሄድ አደግኛ መሆኑ የሚያሳይ ነው ማለታችው የሚታወስ ነው።
አዉሎ ሚድያ ጥር 21/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ