ቻይና ናንጂንግ ሊካሄድ የነበረውን የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አራዘመች

0
151

የአለም አትሌቲከስ አስተባባሪዎች የጂያንግሱ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ናንጂንግ መጪው መጋቢት ወር 2020 ይካሄድ የነበረው የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አሁንም በመቀጠሉ ውድድሩ ለመጋቢት 2021 እኤአ እንዲራዘም ተደርጓል ብለዋል፡፡
ናንጂንግ የአለም የቤት ውስጥ ውድድር ከመጋቢት 13-15 እኤአ 2020 ለማስተናገብ ዝግጅት ስታድርግ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የአለም አትሌቲክስ ባወጣው መግለጫ ቻይና የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጥረት እያደረገች የምትገኝ ቢሆንም ቫይረሱ አሳሳቢነቱ አየጨመረ በመምጣቱ ውድድሩ በዚህ ወቅት በናንጂንግ አይካሄድም፡፡
የአለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ቫይረሱ በበርካታ ሀገራት እየተሰራጨ በመምጣቱ ሁሉም ሀገራት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
በውሃን የተቀሰቀሰው ይህ የኮሮና ቫይረስ ወርርሸኝ እስካሁን 170 ሰዎችን ሲገድል ከ7ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ተይዘዋል፡፡ የአለም አትሌቲክስ አስተዳዳሪዊ አካል ውድድሩን በዚህ አመት ወደ ሌላ ከተማ በማዛወር እንዲከናወን የማድረግ ፍላጎት እንደሌላው አስታውቋል፡፡
የአለም አትሌቲክስ የአለም የቤት ውስጥ ውድድሩ በቀጣይ አመት በ2021 በናንጂንግ ከተማ ለማካሄድ ከናንጂንግ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል ቢቢሲ ስፖርት፡፡
የ2018 የአለም የቤት ውስጥ ውድድር አስተናጋጅ ከተማ የእንግሊዟ በርሚንግሀም ስትሆን የሰርቢያዋ ቤልግሬድ ደግሞ የ2022 ሻምፒዮና እንድታስተናግድ እድሉ ተሰጥቷታል፡፡
አዉሎ ሚድያ ጥር 21/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ