የራሳቸውን ሀይማኖት በሚያስፋፉ ባለስልጣናት የሀገሪትዋ ሰላም እየታወከ ነው ተባለ፡፡

0
1392

የሶማሌ እና የምሰራቅ ሀረርጌ ሃገረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ መቃርዮሰ  በሀረር ከተማ በጥምቀት በአል አከባበር ላይ አጋጥሞ ስለ ነበረው ሁከትና ብጥብጥ አስመልክተው ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ሊቀ ጳጳሱ በመግለጫቸው እንዳሉት በክርስተያኖች ላይ ገሀድ የወጣ እድሎ እየፈፀሙ በሰላም መኖር ስለማይቻል መንግስትም አሰራሩን እንደገና ዞር ብሎ እንዲመለከት  እና ሀገርና ህዝብን ለማስተዳደር የተቀበሉትን ሃላፊነት ህዝብን ለማስለቀስ እና የራሳቸውን ሃማኖት የሚያስፋፉትን ባለስልጣናት እኩይ ድርጊት እንዲያስታግሱልን እንጠይቃለንም ብለዋል፡፡

መንግስት የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ መሪ ፣ፖሊስም የህዝብ ሁሉ አገልጋይ መሆኑ ቢታወቅም በሀገረ-ስብከታችን የተፈፀመው ከዚህ በተቃራኒ በመሆኑ አንዱን እየደገፉ ሌላዉን እያሳደዱ መኖር ስለማይቻል ወደ ፊት ተመሳሳይ ጥፋቶች እንዳይፈፀሙ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ማስገንዘብ እንወዳለን ሲሉ ሊቀ ጳጳስ አቡነ መቃርዮስ መንግስትን አሳስቧል፡፡

አገረ ስብከቱ በመግለጫው ከጥር 10-13 ቀን 2012 ዓ.ም በክርስትያኖች ላይ አካላዊ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል፣የ4 ክርስትያኖች ንብረት ወድሟል ፣17 ክርስትያኖች በግፍ ታስረዋለ፣246 ከርስትያኖች በተፈፀመባቸው ዛቻ እና ማሰፈራርያ፣ድብደባ እንዲሁም ዘረፋ ምክንያት ተፈናቅለው ሀረር በሚገኘው ደብረ አድኅኖ ቅዱሰ ገብርኤል ቤተ-ክርስትያን ተጠግተው እንደሚገኙ አስታውቀዋል ፡፡

መንግስት ለጥያቅያችን አፋጣኝ መልስ ካልሰጠን እና ለፍርድ መቅረብ ያለባቸውን እየተወ የተበደሉትን  ማሰሩንና ማንገላታቱን ከቀጠለ በቤተ-ክርስትያንና በመእመናን ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት አደራጅተን ለመላው የአገራችን ህዝብ ፣መንግስታዊ ለሆኑ እና ላልሆኑ ድርጅቶች፣ ለአለም አቀፍ ተቋማት ማሳወቃችንን እንቀጥላለን ፣በቅርብ ቀንም ሰላማዊ ሰልፍ እንደምናደርግ ለማሳሰብ እንወዳለን ሲሉ አክለው ሊቀ ጳጳሱ ተናግረዋል፡፡

አዉሎ ሚድያ ጥር 20/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ