ስለ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ ያለብዎት ነጥቦች

0
1009

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በቻይና ግዛት ውሀን ከተማ ከ2019-2020 ነበረ ምታየት የጀመረው።

ቫይረሱ ባልተጠበቀ እና ባልታሰበ መንገድ በአጭር ቀን ወደ ተለያዩ የቻይና ከተሞቸ እንዲሁም ወደ ቻይና ጎረቤት ሀገረ ጃፓን መግባቱ የአለም  ብዙሃን መገናኛ ስለ ቫይረሱ በየቀን ሰፊ የዜና ሽፋን መስጠት  ጀመሩ።

ለመሆኑ ካሮና ቫይረስ ምንድን ነው?

አሁን ካሮና ቫይረስ የህክምና ባልሞያዎች ዉሃን ካሮና ቫይረስ እያሉ ለመጀመርያ ግዜ በታየባት ከተማ ስም ይጠሩት ጀምሯል።

ውሃን ካሮና ቫይረስ የቫይረሶች ስብስብ ሲሆን በሰው ልጅ መተንፍሻ አካል ላይ ኢንፌክሽን በመፍጠር ለሞት የሚያበቃ አደገኛ በሽታ ነው። እንዲሁም ስያሜው ያገኘው ከያዘው ቅርፅ ሲሆን  ቫይረሱ አጥቢ እንስሳትና ወፎች  ውስጥም ስለሚገኝ የሰው ልጅ ከእነዚህ እንስሳት ጋር ካለው ቁርኝነት አንፃር የበሽታው አስጊነት ከፍ አርጎታል ይላሉ የዘርፉ የህክምና ባለሞያዎች።

የቻይና የህክምና ባለሞያዎች ባደረጉት ተጨማሪ ምርመራ ይህ ቫይረስ በ ጋማ ከብቶች እና በአሳማ የተለየ ምልክት ያሳያል ነወ ያሉት።

የበሽታው መለያው ከፍተኛ ሙቀት፣ማቅለሽለሽ እንዲሁ ከኒሞንያ እና ከጉንፋን ጋር ተመሳሳይነት ሲኖረው፣በነዚህ እንስሳት ላይ ግን የተቅማጥ አይነት ምልክት ይታይባችዋል ብሏል የህክምና ቡድኑ።

ታድያ የአለም ጤና ድርጅት ይህን ቫይረስ እጅግ አሳሳቢ ሲል ለአለም ህዝብ ስለ ቫይረሱ ሁኔታ ባሳለፍነው ሳምንት አሳውቋል።

ቫይረሱ በአሁን ሰዓት ከቻይና አልፎ የዓለም ስጋት መሆን ከጀመረ ውሎ አድሯል። በቫይርሱ የተጠቁ ሰዎች የሚገኙባቸው ሀገራት ዝርዝር በየግዜው እየተገልፀ ሲሆን ከነዚህ መሃከል፡ ጃፓን፣ ካናዳ፤ ታይዋን፤ ኮትዲቫር ፤ኬንያ ፤አውስትራልያ፣አሜሪካ፣ጀርመን እና ሌሎች በዋናነት ይጠቀሳሉ።

ታድያ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ከየኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር ከሳምንት በፊት በኢትዮጵያ አየር መንግድ ቡኩል ለሚጓጓዙ ሰዎች ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ጀምርያለው ፣እስካሁንም በዚህ ቫይረስ የተጠቃ ኢትዮጵያዊ ዜጋ አለመኖሩ አረጋግጫለው ብሎ ነበር።

የጤና ሚኒስቴርም በዚህ ጉዳይ ትላንት መግልጫ ሰጥቷል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከዚህ በፊት በአጠቃላይ በአለም ደረጃ 581 በቫይረሱ የተጠቁ ሁሙማን ሲኖሩ ከነዚህም 571 ብቻይና እንደሚገኙ ገልፆ የነበረ ሲሆን ፣አሁን ግን የታማሚዎች ቁጥርም ከ አንድ ሺ በላይ ሲሆን፤  እንዲሁም የሟቾች ቁጥር ከ100 በላይ ማሻቀቡን ዘገባዎች ያሳያሉ፡፡

ጤና ሚኒስቴር  ትላንት በሰጠው መግለጫም በካሮና ቫይረስ ሳይጠቁ አልቀሩም የተባሉ ከቻይና ሀገር የመጡ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በአየር መንገድ የቫይረሱ መቆጣጠሪያ ማእከል ማግኘቱን አሳውቋል። የጤና ሚንስትር መግለጫ እንደሚለው በሽታው ከሰው ወደ ሰው የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ በመሆኑ የበሽታው ምልክቶችና ቅድም መከላከያዎቹ ለህበረተሰቡ ይፋ አድርጓል።

በበሽታው የተያዘ ሰው ሃይለኛ ሙቀት፣ማቅለሽልሽ፣እንዲሁም ከፍተኛ የራስ ምታት እና የድካም ስሜት  ይታይበታል፡፡ በተጨማሪም በበሽታው የተያዘ ሰው ለሳንባ ምች ወይም ለኒሞኒያ ይጋለጣል ተብላል፡፡

 እጅን በሳሙና መታጠብ ፣ የአፍንጫ እና የ አፍ መሸፈኛ በመጠቀም ቫይርሱ ቢያንስ ከሰው ወደ ሰው እንዳይተላለፍ ማደረግ ይቻላልም ብሏል።

የተጠቀሙበትን ሶፍት፤ መሃረም፤ጓንት እና ሌሎች ቁሳቁሶች በማቃጠል ወይም በመቅበር የበሽታውን መስፋፋት መግታት ይቻላል ፡፡

ማንኛውም  የበሽታው ምልክት የታየበት  ሰው ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ወይም ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በመሄድ ምርመራ ማድረግ እንዳለበት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ስለ በሽታው በነፃ የጥቆማ  ስልክ መስመር 8335 ማወቅ ፤መጠይቅና መመዝግብ ይቻላል ተብሏል፡፡

አዉሎ ሚድያ ጥር 20/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ