ኮሮና ቫይረስ በአዲስ አበባ

0
517

የኮሮና ቫይረስ ምልክት የታየባቸው አራት ተጠርጣሪዎች መለየታቸውን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ።


ከተለዩት አራት ተጠርጣሪዎች መካከል ሁለቱ የበሽታው ምልክት የታየባቸው ሲሆን ሁለቱ ደግሞ ቫይረሱ በመጀመሪያ መከሰቱ ከታየበት ሁዋን ከተማ የመጡና በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ እንዳላቸው የተጠረጠሩ መሆናቸው ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በበሽታው የተጠረጠሩት ግለሰቦች በሽታው ባይገኝባቸውም ምልክቱ ስለታየባቸው ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው።

በአገር ውስጥ በተደረገ ምርመራ ነጻ መሆናቸው ቢረጋገጥም ሙሉ ለሙሉ ነጻ ስለመሆናቸው ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ የደም ናሙናቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ መላኩን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የኮሮና ቫይረስ የመተንፈሻ አካል የምያጠቃ  የቫይረስ አይነት  ሲሆን ሞትን ሊያስከትል የሚችል አደገኛ በሽታ ነው።

በሽታው ሊተላለፍበት የሚችልባቸው መንገዶችም በ ቫይረሱ የተጠቃ ስው  ሲያስነጥስ ወይም ሲያስል፣ ከታማሚው ሰው ጋር በሚደረግ የቅርብ ንክኪ ናቸው።

በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥ እና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች እንደሚታይባቸውና ።

በሽታው የጠናባቸው ሰዎች ላይ ደግሞ እንደ የሳምባ ምች እና ከባድ የመተንፈሻ አካላት ህመም ይስተዋልባችዋል።

ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ካለብዎ ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ይሂዱ።

የበሽታው ስሜት ከመፈጠሩ አስራ አራት ቀናት በፊት በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ አገራት ሄደው ከነበረም ይህንንም ለጤና ባለሙያ ያሳውቁ።

በሚያስሉበት እና በሚያስነጥሱበት ጊዜ በሽታው ወደ ጤነኛ ሰው እንዳይተላለፍ አፍና አፍንጫን በክንድ፣ በመሃረብ ወይም በሶፍት ይሸፍኑ።

አፍን አፍንጫን ለመሸፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድ እና እጅን ሁልጊዜ በውሃ እና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል።

በበሽታው መያዝዎን ሪፖርት ለማድረግ በነጻ የስልክ መስመር 8335 ወይም የመደበኛ ስልክ 0112765340 መጠቀም ይችላሉ።

አዉሎ ሚድያ ጥር 19/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ