በደቡብ ክልል የክልልነት ጥያቄ የሚያጠናውን ቡድን አባዱላ ገመዳ እንዲመሩት ተመረጡ

0
587

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) በደቡብ ክልል የተነሱ የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት ያቋቋሙትን ኮሚቴ የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስቴር እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት የነበሩት አባዱላ ገመዳ እንዲመሩት ተመረጡ።
ከተለያዩ ብሔሮች የተወጣጡ እና ምሁራንን ያጠቃለለው ይህ ኮሚቴ 80 አባላት ሲኖሩት በክልሉ የተነሱ በደቡብ ክልል የክልልነት፣ የዞንነት፣ ልዩ ወረዳ የመሆን፣ የብሄረሰብ ማንነት ጉዳይ ጨምሮ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የሚቀርቡበትን ለይቶ የሚያቀርብ ኮሚቴ እንደሆነ ታውቋል።
የወላይታ ብሔርን በመወከል በኮሚቴው አባል የሆኑት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምህር አሸናፊ ከበደ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት ግለሰቦቹ የተመረጡት የህብረተሰቡን ጥያቄ ለማቅረብ እና ቅሬታቸውን ለማስተላለፍ ቅርብ በመሆን ወይም ተጽእኖ ፈጣሪ ናቸው ተብሎ በመታመኑ ነው ብሏል።

ከዚህ ቀደም ተሞክሮ ውጤት ያልሰጠ አማረጭን በድጋሚ ማቅረብ ጊዜ መግደል ነውም ብሏል ወብን።
አዉሎ ሚድያ ጥር 19/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ