ድምፃዊ ሙሉዓለም ታከለ የኩላሊት ንቅለ ተከላውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀቀ፡፡

0
606

በመስከረም ወር 2012 መታመሙ ከተነተገረ ጀምሮ በርካታ ድጋፍ እና የገቢ ማሰባሰቢያዎች የተደረገለት ድምፃዊው ለወራት በሃገር ውስጥ በሚገኘው MABD የኩላሊት እጥበት ሲያደርግ ቆየቷል፡፡

የኩላሊት ልገሳውን ከታላቅ እህቱ አግኝቶ ንቅለተከላውን ለማድረግ ወደ ህንዱ አፖሎ ሆሰፒታል ታህሳስ 12 ቀን አቅንቶ የነበረ ሲሆን አሁን ንቅለተከላው በሰላም መጠናቀቁ ታወቋል፡፡

ከህክምና በኋላም ሁለቱም በሙሉ ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆኑ ቀሪ የህክምና ሂደቶች እንደተጠናቀቁም ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለሱ ታውቋል፡፡

ሙሉዓለም ከድምፃዊነቱ በተጨማሪ የግጥምና ዜማ ደራሲ ሲሆን  ፡ ሀመልማሎ፣እኔ እሻላለሁ፣ተሸኒፊያለሁ፣ሽሩረዬ ተወዳጅነት ያገኙ ስራዎቹ  ናቸው፡፡

አዉሎ ሚድያ ጥር 18/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ