‹‹በአዲስ አበባ በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚገኙት የህ.ወ.ሓ.ት ካድሬዎችና የስራ ኃላፊዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እየተነሱ ነው›› ዶ/ር ሰለሞን ኪዳነ

0
159

ከትናንት በስቲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የሚኒስትሮች ሹም ሽር ማድረጋቸው ተከትሎ ህወሓት ባወጣው መግለጫ አባላቱን ከፌደራል ከፍተኛ የሃላፊነት ደረጃዎች እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማንሳት እርምጃ ህግን የጣሰና ችግርም የሚያስከትል ነው ማለቱ ይታወሳል።

ከስልጣናቸው ከተነሱት መካከል የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር የነበሩት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር የሚገኙበት ሲሆን እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የህወሓት አመራሮች የብልፅግና ፓርቲ ካልሆናቹ ተበለው ከስራ እየተሰናበቱ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡  

በተመሳሳይ የህ.ወ.ሓ.ት ከፍተኛ አመራር የሆኑት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊው ሰለሞን ኪዳነ (ዶ/ር) ከስልጣን እንደሚነሱ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ታውቋል፡፡

ይህን ተከትሎ ህወሓት ባወጣው መግለጫ አባላቱን ከፌደራል ከፍተኛ የሃላፊነት ደረጃዎች እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማንሳት እርምጃ ህግን የጣሰና ችግርም የሚያስከትል ነው ብሏል።

ብልፅግና ፓርቲ በበኩሉ የተደረገው የተለመደ ሹም ሽር ስለሆነ ከብሄር እና ከፖለቲካ ጋር ማገናኘት አይገባም ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊው ሰሎሞን ኪዳነ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚገኙት የህወሓት ካድሬዎችና የስራ ኃላፊዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት እየተነሱ በሌሎች አባል ባልሆኑ እየተተኩ  ነው ብለዋል።

“አዲስ አባባ ላይ እንደ ኢህአዴግ ነው የተወዳደርነው። ኢህአዴግ እስካሸነፈ ድረስ ህወሓት 25 በመቶ ቦታ አለው። እኩል የማስተዳደር ስልጣን አለው። ይህንን አሰራር ማፍረስ ማለት የከተማውን መንግሥታዊ አስተዳደር መዋቅር ማፍረስ ማለት ነው” በማለት እርምጃው ህግና ስርዓትን የተላለፈ ነው ይላሉ ምክትል ከንቲባው።

ህ.ወ.ሓ.ት በዚህ ሂደት ውስጥ አካሄዱ ህገ-ወጥ ነው በማለት ብልፅግናን የማይቀላቀል መሆኑንን ማሳወቁ በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መንግስት መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ይበልጥ እንዳካረረው እየተስተዋለ ነው።

አዉሎ ሚድያ ጥር 15/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ