ፍ/ቤቱ እነክርስቲያን ታደለ ተጠርጥረው የተከሰሱበትን ጉዳይ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ችሎት የሚያየው ለአንድ ጊዜ ብቻ መሆኑን ገለጸ

0
172

የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ 13 የወንጀል ተጠርጣሪዎቸን ጉዳይ የሚመለከተው ችሎት አርብ ጥር 8 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸውን በቪዲዮ ኮንፈረንስ እንዲከታተሉ የሰጠው ትዕዛዘ ለአንድ ጊዜ ብቻ መሆኑን ገለጸ፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕዝደንት ክቡር አቶ ተኽሊት ይመስል በሰጡት መረጃ ችሎቱ እነ አቶ ክርስቲያን ታደለ ያሉበትን መዝገብ በዕለቱ የቀጠረው አቃቤ ህግ አዲስ አሻሽሎ ባቀረበው ክስ ላይ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ የነበረ መሆኑን ገልጸው ተከሳሾቹ ወደ ችሎት አዳራሽ ለመግባት ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ቃላቸውን በቪዲዮ ኮንፈረንስ እንዲሰጡ ትዕዛዝ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ባለጉዳዮቹ የሚያደርጉትን ክርክር እና ምስክር ቃል የመስማት ሂደትን በመደበኛው የችሎት አዳራሽ እንደሚያካሂድ ም/ፕሬዝደንቱ ገልጸዋል፡፡

ተጠርጣሪ ተከሳሾቹ ወደ ችሎት አዳራሽ አንገባም ለማለት የመጀመሪያ ምክንያት ያደረጉት፤ ደጋፊዎቻችን ወደ ችሎት እንዳይገቡ ተከልክለዋል የሚል ሲሆን ምክትል ፕዝደንቱ የችሎት አዳራሹ ሊይዝ የሚችለውን ያክል ሰው ይዞ እንደነበርና የችሎቱን ሂደት ለመከታተል በዕለቱ የተገኘው ሰው ብዙ በመሆኑ ወደ አዳራሹ መግባት ያልቻሉት ውጪ እንዲቆዩ ተደርገዋል ብለዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ወደፊትም ችሎቱ መደበኛ ሂደቱን ሊያከናውን የሚያስችለውን ያክል የሰው ቁጥር በችሎት አዳራሹ እንደሚታደም በመግለጽ የታዳሚው ቁጥር ከአዳራሹ አቅም በላይ በሚሆንበት ጊዜ ከአዳራሹ ውጪ እንዲቆዩ ይደረጋል ሲሉ ክቡር አቶ ተኽሊት ይመስል አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል ተከሳሾቹ ደጋፊዎቻችን በፖሊስ ጥቃት ደርሶባቸዋል በማለት ወደ ችሎት አዳራሽ ለመግባት ፈቃደኛ አለመሆቸው ተጠቁሟል፡፡ ለዚህም የፍርድ ቤቱ አመራር ጉዳዩን አጣርቶ እርምጃ እንደሚወስድ ቢገልጽም ተጠርጣሪዎቹ የሃሳብ ለውጥ ባለማድጋቸው ችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ለመስጠትና የእምነት ክህደት ቃላቸውን በቪዲዮ ኮንፈረንስ እንዲሰጡ ትዕዛዝ መስጠቱ ታውቋል፡፡

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

አዉሎ ሚድያ ጥር 13/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ