የአነ አስክንድር ነጋ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ አገኘ

0
282

ፓርቲው ጥር 4 ቀን 2012 ዓ.ም ጊዚያዊ የምዝገባ ፈቃድ ማግኘቱን ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ታውቋል፡፡
ፓርቲው ሳንፈልግ፣ በሁኔታዎች አስገዳጅነት የተመሰረተ ነው ያሉት የፓርቲው መስራች አቶ እስክንድር ነጋ ፤እስካሁን በየጊዜው ስብሰባዎችን እንዳናደርግ፣ሰላማዊ ሰልፍ እንዳናከናውን፣ዴሞክራሲያዊ መብቶቻችን ታፍነው ነበር ብለዋል፡፡

እንደምክንያት ይቀርብ የነበረውም ህጋዊ ቁሙና የላችሁም የሚል ነበር ያሉት አቶ እስክንድር ፣ ከአሁን በኋላ ግን እንደዚህ አይነት ሰበብ ሊቀርብ አይችልም በማለት ተናግረዋል፡፡


ፓርቲው ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ መደረግ እንዳለበት እንደሚያምን ፣ ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የማድረግ ጉዳይ በሁለተኛ ደረጃ ፣ ምርጫ የማድረጉ ነገር ደግሞ በቀዳሚነት እንደተያዘ ምልክቶች እየታዩ ነው ይህ ተገቢ አይደለም በማለት አቶ እስክንድር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል፡፡

 በተጨማሪም  በሃገር አቀፍ ደረጃ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል ባለመሆኑ የወጣው ጊዜያዊ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ይህንን ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው ብለዋል።


በመሆኑም ምርጫ ለማድረግ  የሃገሪቱ ጸጥታ ዋና መስፈርት መሆን ይገባል ። ይህ ሳይደረግ ወደ ምርጫ ከተገባ ግን ወደ ነበርንበት አዙሪት ስላሚመልሰን ምርጫው ሊራዘም ይገባል ብለዋል።


ፓርቲው ክልላዊ የፓለቲካ ፓርቲ ሆኖ ነው ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃዱን ያገኘው።
ሆኖም ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ጥምረትም ፣ቅንጅትም የመመስረት ውጥን እንዳለውም ይፋ አድርጓል።


የፓርቲው ፖለቲካዊ መስመር ቀኝ ዘመም እንደሚሆን፣ በዚህ ስኬታማ ከሆኑ አለም ላይ ካሉ በተለይ የአውሮፓ ቀኝ ዘመም የፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር አብሮ መስራት የሚያስችል ሁኔታዎችንም አስበው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ፓርቲው አስታውቋል።
ለ11 ወራት የፖለቲካ ስራ ሲያከናውኑ መቆየታቸውንም አቶ እስክንድር ነጋ አመልክተዋል።


ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላ ከጥር 16 እስከ የካቲት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ይከናወናል።

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ጠንካራ ታዛቢዎች እና አስፈጻሚዎች እንዲኖሩ ህዝቡ የበኩሉን ሊወጣ ይገባልም  ብሏል።

በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ ፌርማ ለፓርቲው የተሰጠው ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ፣የፖለቲካ ፓርቲውን ለማስመዝገብ የሚያስፈልጉ ተግባራትን ለማከናወን ብቻ የሚያገለግል ሲሆን የአገልግሎት ጊዜውም ሶስት ወራት ብቻ ነውም ተበሏል።


ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ በሚቀጥሉት 15 ቀናት ውስጥ መስራች ጉባኤ በማድረግ ህጋዊ ፍቃዱን እንደሚይዝ መገለጹን ዶቼ ቨለ ነው ዘገበው፡፡

አዉሎ ሚድያ ጥር 13/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ