በኦሮሚያ ክልል አርሲ አቦምሳ በተቀሰቀሰ ግጭት ምክንያት የጥምቀት በአል አንድ ቀን አልፎ ዛሬ ተከበረ፡፡

0
209

አርሲ አቦምሳበ 10/04/2012 ዓ/ም የከተራ በአል እለት  በተከሰደተ ግጭት ምክንያት በአሉ በእለቱ መከበር አልቻለም ነበር፡፡

በከተራ ቀን ታቦታት ወደ ወንዝ መውረድ ስላልቻሉ እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ምክንያት ነው በአሉ በዕለቱ ማክበር ያልተቻለው ተብሏል፡፡

በአካባቢው ታሪካዊ ናቸው የሚባሉት የመድሐኒ ዓለም እና የመጥምቁ ቅዱስ ዮሀንስ ታቦታትን የከተራ እለት ማንቀሳቀስ ባለመቻሉ ትናንት  ወደ ጥምቀተ ባህር ወርደው ያደሩ ሲሆን ዛሬ በአሉ ተከብሮ በሰላም ወደ መንበራቸው ተመልሰዋል፡፡

 ችግሩ ከተፈጠረ በኋላ የመከላከያ ሰራዊት አባላት  በአካባቢው በመሰማራታቸው የተፈጠረው ችግር ከፍተኛ ጉዳት አላደረስም ተብሏል፡፡

 በአርሲ አቦምሳ የጥምቀት በአልን ምክንያት አድርጎ የተፈጠረው አለመረጋጋት ተወግዶ  አሁን ሙሉ በሙሉ ወደ ሰላምዊ እንቅስቃሴ ተገብቷል ተብሏል፡፡

አዉሎ ሚድያ ጥር 12/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ