በሀረሪ ክልል የጥምቀት በዓልን ምክንያት አድርጎ በተፈጠረ ግጭት ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል

0
101

የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረመዳን ኡመር በሰጡት መግለጫ ከጥር 10/2012 ጀምሮ አንዳንድ የጥፋት ተልዕኮ ያነገቡ አካላት በዓሉ በሰላም እንዳይከናወን ጎራ ለይተው ግጭት ለማስነሳት ጥረት እንዳደረጉ ገልፀዋል።
በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሳቢያም በአራት(4) ሲቪል ዜጎች እና በአስራ አምስት (15) የፀጥታ አካላት ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን እንዲሁም በንብረት ላይም ከፍተኛ የሆነ ጉዳት መድረሱን ለኮሚሽኑ የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።
በተጨማሪም በሰውና በንብረት ላይ የደረሱ ጉዳቶችን በሚመለከት ፖሊስ አስፈላጊውን የማጣራት ስራ በማከናወን እንዲሁም ድርጊቱን የፈፀሙ አካላትን በማጣራት ለህግ እንደሚያቀርቡና ስለጉዳዩም በዝርዝር ለህዝቡ እንደሚያሳውቁ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።
ምንጭ፦ የሀረሪ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን

አውሎ ሚዲያ ጥር 12/2012 ዓ ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ