ኢንጀነር ታከለ ኡማ የአዲስ አበበ ከተማ ፖሊስን ለማስተዳዳር እንዲፈቀድላቸው የፓርላማውን እገዛ ጠየቁ፡፡

0
413

ደመወዝ ከመክፈል ውጪ ከተማ አስተዳደሩ እንደማያስተዳድረው ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተናገሩ፡፡

ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ካቢኔያቸው ከሕዝብ ተወካዩች ምክር ቤት አባላት ጋር ውይይት አካሂደዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በከተማዋ የሚሰተዋለውን የተደራጀ ወንጀልና ዘረፋ ህብረተሰቡ ኑሮ ላይ ጫና እያሳደረ ነው ከተማዋ አስተዳድር ምን እየሰራ ነው የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

ኢንጅነር ታከለ ለተነሳላቸው ጥያቄ የአዲስ አበባ ፖሊስ እኛ ደመወዝ ከመክፈል ውጪ ሌላ ሃላፊነት የለንም የከተማዋን ፖሊስ የሚመራው ፌደራል ፖሊስ ነው ብለዋል፡፡

የከተማዋን ፖሊስን መምራት ባንችልም የከተማው ጸጥታ ስለሚመለከተን ወጣትና ነዋሪውን የአካባቢውን ፀጥታ እንዲያስከብርና እንዲጠብቅ እንደገና እንዲደራጁ አድርገናል ብለዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም እንደዘገበው የከተማዋን ፖሊስ ለማስተዳደር ሙሉ በሙሉ ሃላፊነት ባይሰጠን እንኳን የፌደራል ፖሊስን ውክልና ስጡን እና እንምራ ብለን ጥያቄ ብናቀርብም አልሰጡንም ችግሩን ለመፍታት የፓርላማውም ድጋፍ ያስፈልገናል ብለዋል ኢንጅነር ታከለ፡፡ አዉሎ ሚድያ ጥር 09/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ