ባለፉ ሁለት ወራት ውስጥ በዩኒቨርሲቲዎች በተፈጠሩ ግጭቶች 12 ተማሪዎች ተገድሏል

0
70

መንግስት ግጭቶች በተከሰቱባቸው 21 ዩኒቨርስቲዎች ፌደራል ፖሊስ ከላከ ጀምሮ ባለው ሁለት ወራት ውስጥ ያለውን ሁኔታ ሪፖርት ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሪፖርት ለህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዩች የሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ አቅርቧል።

የቋሚ ኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ አቶ ጫላ ለሚ ባለፉት ሁለት ወራት 12ተማሪዎች መገደላቸውን አስታውቀዋል።

ለሚከሰቱት ግጭቶች የዩኒቨርስቲ አመራሮች፤ የአኣተዳደር ሰራተኞች እና መምህራን ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ ተገኝተዋል ብሏል። ስለተወሰዱ እርምጃዎች ግን ምንም የተባለ ነገር የለም።

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከዚህ በፊት የዩኒቨርሲቲዎች ሰላም እጦት አስመልክተው ባደረጉት ንግግር እስከ መዘጋት የሚደርስ እርምጃ እንወስዳለን ማለታቸውን ተከተሎ አንዳንድ ሙሁራን ዩኒቨርሲቲ መዝጋት መፍትሄ አይሆንም ማለታቸው  የሚታወስ ነው፡፡

ዶቼ ቨለ እንደዘገበው

አዉሎ ሚድያ 09/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ