የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት ፕሮግራም ለአራት ክልሎች ለወተት ማጓጓዣ የሚውሉ መኪናዎችን ሰጠ

0
657

በግብርና ሚኒስቴር የወተት ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር 10 ሺህ ሊትር ወተት መያዝ የሚችሉ ቦቴ መኪናዎችን ለአራቱ ዋና ዋና ክልሎች ለአማራ፣ ለኦሮሚያ፣ለትግራይና ለደቡብ ተበርክቷል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ የሆኑት ዶ/ር ገ/እግዚአብሄር ገ/ዮሃንስ የመኪና ርክክቡን አስመልክቶ እንደገለጹት መንግሰት ላለፉት ዓመታት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት ከሚገኙት ዘርፎች አንዱ የተቀናጀ የኢንዱስትሪ ፓርክ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም በአራት ክልሎች ግንባታ መካሄዱን ያነሱ ሲሆን ዓላማቸውም የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ በተለይም ምርትና ምራታማነት ላይ እሴትን በመጨመር ለገበያ ማቅረብ እና አርሶ አደሩ ተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ ማድረግ  ነው ብለዋል፡፡

በዘርፉ የስራ እድል መፍጠር ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስት ድኤታው  የተበረከቱት መኪናዎችም ከማህበራት ወተትን በመሰብሰብ ለወተት ኢንዱስትሪ ፓርኮች በማቅረብ የገበያ ትስስርን ይፈጥራሉ ብለዋል፡፡

አውሎ ሚዲያ ጥር 08/2012 ዓም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ