ፕሬዝዳንት ትራምፕ “ኢትዮጵያን ያዳንኳት እኔ ነኝ” ሲሉ ተናገሩ፡፡ –

0
201

ፕሬዚዳንቱ ትላንት ባደረጉት የምርጫ ቅስቀሳ ዶክተር አብይ አህመድ ሃገሪቱን ስላዳነ ተብሎ የኖቤል ሽልማቱ የተሸለመው በእኔ ምክንያት ነው ብሏዋል፡፡

“አንዲትን ሀገር ለማዳን አንድ ስምምነት ፈፀምኩ፤ ሀገሪቱን አዳንኳት። የሀገሪቱ መሪ ሀገሪቱን ስላዳነ ተብሎ የሰላም ኖቤል መሸለሙን ሰማሁ። ለነገሩ እውነቱን እኛ ካወቅነው በቂ ነው።” ሲሉ ነው ፕሬዚዳንት ትራምፕ የተናገሩት፡፡
ፕሬዚዳንቱ ይህንን ይበሉ እንጅ ኢትዮጵን ከምን እንዳዳኗት በግልፅ አልተናገሩም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2019 የኖቬል ሽልማትን ሲያሸንፍ ባደረጉት ንግግር በዋናነት ኢትዮጵያ እና ኤርትራን በማስማማታቸው ሽልማቱን እንዳነኙ ተናግረዋው ነበር፡፡

የኖቤል ሽልማት ድርጅት በበኩሉ ሽልማቱን ለዶክተር አብይ የሰጠው በኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ እና በሀገር ውስጥ ላከናወኗቸው የሪፎርም ስራዎች እንደሆነ በዝርዝር አሳውቆ ነበር፡፡
የፕሬዚዳንት ትራምፕ ንግገር ግን የውጭ ሃይሎች በተለይም አሜሪካ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ጣልቃ ገብነት ፈጥረዋል ለሚልው ንግግር እንደማጠናከሪያ የሚቆጠር ነው፡፡

ከሰሞኑ በተካሄደው የህወሓት አስቸኳ ጉባኤ ማጠቃለያ መግለጫ ላይ የውጪ ሃይሎች በኢትዮጵያ ላይ ያደርጉትን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙ እና ሃገሪቱን ወደ ከፋ መንገድ እየሄደች ስለሆነ የዚህ ተባበሪ ከመሆን እንዲቆጠቡ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ታዋቂው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው ከአውሎ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ በአሁኑ ሰአት የውጪ ሃይሎች ጣልቃገብነት ከምንግዜውም ባለይ እየበዛ ነው ማለታቸውም ይታወሳል፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናንድ ትራምፕ የሰላም ኖቤል ሽልማቱ እሳቸው ላዳኗት ኢትዮጵያ መሪ መሰጠቱን ይናገሩ እንጅ ስለ ጉዳዩ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ግን እስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡

አውሎ ሚዲያ ጥር 1/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ