ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የደበቡ አፍሪካውን ፕሬዚዳንት በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት እንዲያግዟቸው ጠየቁ

0
176

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የደቡብ አፍሪካውን ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳን በህዳሴ ግድብ ምክንያት በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለመፍታት እንዲያግዟቸው ጠይቀዋል፡፡
እንደ SABC News ዘገባ ሲሪል ራማ ፎሳ ውጥረቱን ለመፍታት ጣልቃ እንዲገቡ ነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የተጠየቁት!

በህዳሴ ግድብ ላይ የሚደረገው ድርድር ካለ ስምምነት የተቋጨ ሲሆን በነገው እለት የሶስቱ ሀገራት ሚኒስትሮች ዳግሞ በአሜሪካ ለአሜሪካ መንግስት ሪፖርት ያቀርባሉ፡፡

ድርድሩ ባለመሳካቱ በሀገራቱ መካከል ሶስተኛ አ አደራዳሪ አካል እንዲገባ ሊደረግ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል!
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግብፅ በትላንትናው እለት በሁሉም የወታደራዊ ዘርፎች ላይ ሙሉ የልምምድ እንቅስቃሴ ጀምራለች! እንቅስቃሴው ለመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ተ|ክሎ ነው ይባል እንጅ በግልፅ ግን አልታወቀም!

አውሎ ሚዲያ ጥር 3/2912 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ