የዜግነት ፖለቲካ የሚባል አለ ወይ. . .?

0
246

(ወልደጊዮርግስ ገብረሂወት)

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዜጎች የሆኑ ሁሉ ስለ ሀገራቸው ፖለቲካ ይደራጃሉ፣ በሃይልም ሆነ በምርጫ ስልጣን ለመያዝ ይመኛሉ፣ ይሰራሉ። ስለዚህ የዜግነት ፖለቲካ የሚባል ካለ ዜጋው በፈቀደው መልክ ሃሳቡን በመግለጽ በፖለቲካው ይሳተፋል፣ ይደራጃል ማለት ነው። የብሄር ፖለቲካ ሆነ -ብሄር ዘለል ፖለቲካ ሁሉ በዜግነቱ የሚጎናጸፈው የፖለቲካ ተሳትፎ መብት ነው። በዜግነቱ ተከብሮ እንዲኖር በፈለገው መንገድ መደራጀቱ ነው።

“የዜግነት ፖለቲካ“ ብሎ የተለየ መደብ (የመደራጀት ዓይነት) ያለ ማስመስል-ትርጉም ያለው ውይይት አይደለም። በአውሮፓም ሆነ በአሜሪካ “የዜግነት ፖለቲካ“ እንደሚባለው ከሆነ ግን ዜግነት ለማግኘት የሚደረገው የስደተኞች እንቅስቃሴ እንዲሁም ስደተኞችን ዜጋ ለማድረግምን ለመከልከልም ከሚወጡት ህጎችና አዋጆች ጋር ተያይዞ በሀገራቱ መንግስታትና ፖለቲከኞች የሚነሱ የፖለቲካ ክርክር ነው። የዜግነት ፖለቲካ የሚባለው የሀገራቱን ፓስፖርት ለማግኘትና ላለመስጠት የሚደረገው ፖለቲካዊ ግብግብ ነው።

ስለዚህ ጉዳዩ በኢትዮጵያ አውድ ሲታይ ህጋዊ ዜግነታችን እውቅና የለውም፣ እንደዜጋ እንቆጠር ወይም እንደዜጎች አልተቆጠርንምና እውቅና ይሰጠን ከሆነ ሌላ ክርክር ነው። ግን ኢትዮጵያዊ ሆኖ የዜግነት መብት የሚነፈግ የለም (ወይም የሁሉም ጎደሎ ነው)። በግለሰብነት ደረጃ ማንነትን የማስጠብቅ ሙግት ከሆነ ደግሞ አሁንም በማንነት ፖለቲካ ውስጥ የሚወድቅ ይሆናል።

አለበለዚያ ብሄሮችም ዜጎች ናቸው። የዜጋ ፖለቲካ ኣቀንቃኞች ሃሳብ ልክ ኦሮሞ ፣ ኣማራ፣ ትግራይ እንደሚባለው ማንነት “ኢትዮጵያዊ“ የሚባል “ብሄር“ በፌደሬሽን ምክር ቤት እውቅና ኣልተሰጠውምና እንደዜጋ እውቅና ኣልተሰጠንም የሚል መልእክት ያዘለ ይመስላል። ግን እሱ የማንነት እውቅና እንጂ የዜግነት እውቅና አይደለም። ሁሉም ማንነቶች በኢትዮጵያዊ ዜግነት ጥላ ስር ያሉ ናቸው።

ጥር 5 ፣2012

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ